Land Lease & Real Estate

የሐረሪ ሕዝብ ክልላዊ መንግሥት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ባለሥልጣን የከተማ ቦታዎች የሊዝ ጨረታ ሰነድ ማቅረቢያ ጊዜን ለማራዘም ይፈልጋል

Description

የከተማ ቦታዎች የሊዝ ጨረታ ሰነድ ማቅረቢያ ጊዜን ስለማራዘም የወጣ ማስታወቂያ

የሐረሪ ሕዝብ ክልላዊ መንግሥት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ባለሥልጣን በአዋጅ ቁጥር 721/2004 መሠረት በሐመሬሳ ኢንዱስትሪ ዞን፣ በኤስ ኦ ኤስ፣ በሪፍቲ ቫሊ፣ በገስት ሀውስ፣ በቀላዳንባ ኮንዶሚኒያም አና በደከር የቀድሞ ኬላ አካባቢ የሚገኙ ከቅይጥና ከኢንዱስትሪ አገልግሎት የሚውሉ ቦታዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስተላለፍ መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም ባወጣው ማስታወቂያ ጨረታ መከፈቱ ይታወሳል።

ሆኖም ተወዳዳሪዎች አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉና ሰፊ የምዝገባ እድል ለመስጠት ሲባል የጨረታ ሰነድ መግዣ፣ መመለሻና መክፈቻ ጊዜ ከተጨማሪ 10 የሥራ ቀናት ማራዘም አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።

በዚሁ መሠረት፦ የጨረታ ሰነድ ሽያጭና መመለሻ የመጨረሻ ቀን፦ እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ድረስ ተራዝሟል።

የጨረታ ሳጥን የሚዘጋበት ጊዜ፦ ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ላይ ይሆናል።

የጨረታ ሳጥን የሚከፈትበት ጊዜ፦ ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ 4ኛ ፎቅ አዳራሽ ይከናወናል።

ከዚህ ቀደም በጨረታ ማስታወቂያው ላይ የወጡት የCPO መጠን (5%)፣ አነስተኛ የቅድመ ክፍያ መጠን (30%)፣ የሰነድ ዋጋ (1,500.00 ብር) አና የማወዳደሪያ መስፈርቶች (80/20) አንደተጠበቁ ናቸው።

የሐረሪ ሕዝብ ክልላዊ መንግሥት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ባለሥልጣን

ከዚህ በፊት የወጣውን ጨረታ ለመመልከት እባክዎን ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ

https://tenders.qelal.et/tender-6ab247800a538abcc2000001/ 


Tender details

  • Deadline: 2026-10-20
  • Bid closing time: 09:00
  • Bid opening: 2026-10-20 10:00
  • Region: Hareri
  • Publishing entity: Harari City Government City Development Construction Office
  • Bid bond: 5%
  • Bid document price: 1,500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 05, 2026)
  • Posted at: 2026-10-06T09:53:32.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders