Food Items and Drinks
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አሰተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን አገልግሎት ለሚሰጣቸው መ/ቤቶች በ2019 በጀት ዓመት የሚያስፈልጋቸውን የሠራተኛ ዳቦ ቤት አገልግሎት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል
Description
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ፤
የግዥ መለያ ቁጥር 002/2019
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አሰተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን አገልግሎት ለሚሰጣቸው መ/ቤቶች በ2019 በጀት ዓመት የሚያስፈልጋቸውን በአንድ/ ሎት ማለትም፡-
- ሎት 1- የሠራተኛ ዳቦ ቤት አገልግሎት፣
ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርት አሟልቶ በጨረታው መወዳደር ይችላል።
1. በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ ንግድ ምዝገባ ምስከር ወረቀት ያላቸው፣ ግብር ከፋይነት ምዝገባ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ ከግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት አቅራቢነት ማስረጃ ያለው፣ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ተመዝጋቢ የሆነ፣
2. በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ እንዲሁም በ2018 በጨረታ መሳተፍ የሚችሉ መሆናቸው ከሚመለከተው ግብር ሰብሳቢ አካል በጨረታ መሳተፍ እንዲችሉ የሚሰጥ የታደሰ የምስክር ወረቀት /ክሊራንስ/ ማቅረብ የሚችሉ
3. የጨረታ ማስከበሪያ፡- ለእያንዳንዱ ሎት ከአጠቃላይ ለበጀት ዓመቱ ከተበጀተው በጀት ከ0.5-2% የተሰላ ነው።
4. የባንክ አካውንታ ያላቸው
|
ሎት 1 |
|
10,000.00 |
5. በእያንዳንድ ሎት ለብቻው በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ADDIS KETEMA SUB CITY ADMINSTRATOIN PUBLIC SERVICE & HUMAN RESOURECE DEVELOPMENT OFFICE PURCHASING ADMINISTRATION SUPPORTIVE PROCESS በሚል ስም የተሰራ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
6. የሚታዘዘው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ተቀባይነት የሚኖረው የሲፒኦ ቁጥር የሚታይ ከሆነ፣ የተጫራቹን ስም በግልፅ የሚነበብ ከሆነ ሲፒኦ ጀርባ ላይ የባንኩ ማረጋገጫ ማህተም ያለው ከሆነ ብቻ ነው።
7. ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10/አስር/ የሥራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር / በመከፈል የጨረታውን ሠነድ በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡ 30 እስከ 11፡30 በአ/ከ/ክ/ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የፋይናንስ ቡድን 6ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 605 መውሰድ ይችላሉ።
8. በክፍል 6 ባዶ በቴክኒክ መመዘኛዎች ላይ ተሟልቶ፣ ተፈርሞ እና ማህተም ተደርጎ፣ በሁሉም ገጽ ላይ ተፈርሞ የድርጅቱ ማህተም ተደርጎ ሙሉ የጨረታ ሰነድ / መመሪያ| ተመላሽ ይደረጋል።
9. የጨረታ ሰነዱ ቴክኒካል ዋናውን አንድ// እና ፎቶ ኮፒ// ፋይናንሺያል ሰነድ ዋናውን አንድ// እና ፎቶ ኮፒ አንድ/ ለየብቻ በፖስታ ታሸጎ በድምሩ አራት/4/ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ኦርጅናል/ኮፒ ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል በሚል በፖስታው ላይ በመግለጽ በመፃፍ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን አ/ከ/ክ/ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን 6ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 605 ማስገባት ይኖርበታል።
10. የጨረታ ሰነድ ለመግዛት እና ፖስታውን ለማስገባት ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ እስከ 10ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 11፡30 ድረስ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 605 ማስገባት ይችላሉ። በ11ኛው የስራ ቀን ጠዋቱ 3፡00 የጨረታው ሳጥን የሚታሸግ ሲሆን በዚሁ ቀን ጠዋቱ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፤ ነገር ግን 11ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
11. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ ፡- 011-827-9979 /011-895-9223 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል፤
አድራሻ፡- አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ከግሩም ሆስፒታል ከፍ ብሎ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የፋይናንስ ቡድን፤ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 605
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና
የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን
Tender details
- Deadline: 2026-10-16
- Bid closing time: 09:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን ጠዋቱ 3፡00
- Bid opening: 2026-10-16 09:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን ጠዋቱ 3፡30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት
- Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Oct 06, 2026)
- Posted at: 2026-10-06T10:56:00.000Z
- Source: Qelal Tenders