Building Construction
ዘ ብሩክ ሆስፒታል ፎር አኒማልስ በዚህ ዓመት በባህር ዳር ከተማ የእንሰሳት ጤና እና እንክብካቤ ማዕከል ግንባታ ስራ ለማሰራት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ዘ ብሩክ ሆስፒታል ፎር አኒማልስ በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በቁጥር፡ 0883 የተመዘገበ መንግስታዊ ያልሆነ ግብረሰናይ ድርጅት ሲሆን ከተመዘገበበት ጊዜ ጀምሮ ዋና ቢሮውን አዲስ አበባ በማድረግ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡ የድርጅቱ አላማ የጋማ እንስሳትን ደህንነትና ጤንነት ማሻሻል እና በእነዚህ የጋማ እንስሳት ጉልበት ኑሯቸውን የመሰረቱ የማህበረሰብ ክፍሎችን የኑሮ ሁኔታ ማሻሻል ሲሆን ይህንንም ለመተግበር ከመንግስት የእንስሳት እና የግብርና ተቋማት ጋር በትብብር ይሠራል፡፡
ድርጅታችን በዚህ ዓመት በባህር ዳር ከተማ የእንሰሳት ጤና እና እንክብክቤ ማዕከል ግንባታ ስራ ሎት አንድን ለመስራት ይፈልጋል፡፡
ይህንንም ለማከናወን ድርጅታችን ብሩከ ኢትዮጵያ ብቁ እና መስፈርቶችን የሚያሟሉ ልምድ ያላቸው ደረጃ አምስት ጠቅላላ/ህንጻ ስራ ተቋራጭ እና ከዚያ በላይ (GC/BC Five and above) የጨረታ ሰነዶችን በታሸገ ኤንቨሎኘ በማቅረብ እንድትወዳዳሩ ይጋብዛል፡-
| የጨረታ ቁጥር | የፕሮጀክቱ ስም | ከተማ | የስራው አይነት |
| 1-የባህር ዳር ከተማ የተቀናጀ የእንሰሳት ጤና እና እንክብካቤ ማዕከል ሎት 1 | |||
| ሀ-በአማራ ክልል | |||
| B-ETH/15/2026 | Bahir Dar Integrated Animal Health and welfare center lot 1 | Bahir Dar Urban Administration | Shelter Block and Fence Work |
1) ተጫራቾች ህጋዊና የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (የቫት) ተመዝጋቢ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡ (የጨረታ ሰነድ ስትገዙ ማቅረብ ይጠበቅባቹሃል)፡፡
2) ተጫራቾች የተሟላ የጨረታ ሰነዱን በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 3፡ዐዐ ሰዓት እሰከ 1ዐ፡ዐዐ ድረስ አዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 የቤት ቁጥር 797 ከሚገኘው የድርጅታችን ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 600.00 (ስድስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
3) ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላው የጨረታ ዋጋ 2% ቦንድ በሲፒኦ መልክ ብቻ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ሲፒኦው የጨረታ ኤንቨሎኘ ውስጥ ለብቻ ታሽጎ መቅረብ አለበት፡፡ የቀረበው ሲፒኦ ከሂሳብ ስሌት ማስተካከያ በኋላ ለሚመጣው ጠቅላላ ዋጋ የ2%ቱን ከ20% በታች ከሆነ ተጫራቹ ከውድድር ውጪ ይደረጋል፡፡
4) ተጫራቹ አሸናፊ ከሆነ ለቅድመ ክፍያ የሚሆን የሁኔታዎች ያልተወሰነ (Unconditional Bank Guarantee) የባንክ ዋስትና 30% ማቅረብ የሚችል መሆን ይጠበቅበታል፡፡
5) ተጫራቾች የታሸገውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በ 2merkato.com ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 21 ቀናት ውስጥ ከላይ በተ.ቁ. 2 በተጠቀሰው አድራሻ በሚገኘው የብሩክ ጽ/ቤት ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በ21ኛው ቀን ከቀኑ 7፡30 ሰዓት ሲሆን የጨረታ ማቅረቢያው 21ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀናት ከዋለ የጨረታ መዝጊያው ቀን በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከቀኑ 8:00 ይሆናል᎓᎓ ከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ውጭ የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
6) ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በተዘጋበት ቀን በተ.ቁ. 5 እንደተመለከተው ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ይከፈታል።
7) ድርጅቱ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የጨረታ መክፈቻውን ቀን የማራዘም ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ እንዲሁም ቀደም ብሎ በድርጅቱ ሥራዎች ላይ ዝቅተኛ አፈፃፀም ያላቸውን የጨረታ ተወዳዳሪዎች ከጨረታው እንዳይሳተፉ ማድረግ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
8) ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-661-0069/011-662-1885 በመደወል ወይም በኢሜይል [email protected] አድራሻችን መጠየቅ ይቻላል፡፡
አድራሻችን፣ 22 ማዞሪያ በአውራሪስ ሆቴል ፊት ለፊት ከቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል በጀርባ ባለው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል ወደ 24 በሚወስደው መንገድ ላይ በንጋት ህንፃ እና በአዳነ ገብሩ ህንፃ በኩል ወደ ውስጥ ገባ ብሎ፡፡ ስልክ 011-661-0069/011-662-1885
Tender details
- Deadline: 2026-10-27
- Bid closing time: 13:30
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በ 2merkato.com ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 21 ቀናት ከቀኑ 7፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-27 14:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በ 2merkato.com ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 21 ቀናት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: The Brooke Hospital For Animals
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 600.00 ብር
- Published on: Qelal Tenders (Oct 07, 2026)
- Posted at: 2026-10-07T07:35:47.000Z
- Source: Qelal Tenders