Vehicle
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የተለያዩ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ኢ.ኘ.ድ 010/2019
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተገለጹትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም፡- ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
- በዘርፉ ለዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው
- የንግድ ምዝገባ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት
- የቫት ሰርተፍኬት
- በመንግስት ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገበ
- ሎት-1. የመኪና ሰርቪስ እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ መጠን 254,503.60 (ሁለት መቶ ሃምሳ አራት ሺህ አምስት መቶ ሶስት ብር ከ60/100 ሳንቲም)
- ሎት-2 የጅግጅጋ ከተማ የህትመት ስርጭት የመኪና ኪራይ ለአንድ አመት በውል የሚሰራ የጨረታ ማስከበርያ መጠን 120,000.00 (አንድ መቶ ሃያ ሺህ ብር)
- ሎት 3 የሲዳማ ክልል ህትመት ስርጭት የመኪና ኪራይ እና የሞተር ሳይክል ኪራይ ለአንድ አመት በዉል የሚሰራ የጨረታ ማስከበሪያ መጠን 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)
- ሎት 4 ልዩ ልዩ የመስተንግዶ ማቅረቢያ ዕቃዎች የጨረታ ማስከበርያ መጠን 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)
በሲ.ፒ.ኦ ወይም ቢድቦንድ ወይም ለጥቃቅንና አነስተኛ ከአደራጃቸው አካል የሚሰጥ የዋስትና ደብዳቤ በማያያዝ ይህ ጨረታ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 15 ተከታታይይ ቀናት አንደኛ ፎቅ በሚገኘዉ አቅርቦት መምሪያ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ቴክኒካል ዶክመንት ዋና እና ቅጂ እንዲሁም የሚወዳደሩበትን ዋጋ ዋና እና ቅጂ በሚል በጉልህ በሚታይ መልኩ በመጻፍና የሚወዳደሩበትን ሎት በፖስታዎቹ ላይ በመግለጽ በአራት የተለያየ ፖስታ በማሸግ ማስገባት የሚኖርባቸዉ ሲሆን የጨረታ ማስከበሪያ ቴክኒከ ዋና ሰነድ ፖስታ ዉስጥ ተያይዞ መገኘት አለበት።
- በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ 100 ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ስርዝ ድልዝ ያለውና ያልተፈረመ እንዲሁም በጉልህ የማይታይ አጠራጣሪ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 4፡30 በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አቅርቦት መምሪያ 1ኛ ፎቅ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን የተጫራቹ አለመገኘት ጨረታውን ከመከፈት አያስተጓጉለውም።
- የጨረታ መክፈቻው ቀን እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ ባለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
- ድርጅታችን አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ፊት ለፊት
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-10-22
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ጨረታው በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-22 10:30
- Bid opening (note): ጨረታው በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Press Agency
- Buyer address: አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ፊት ለፊት
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 07, 2026)
- Posted at: 2026-10-08T10:14:45.000Z
- Source: Qelal Tenders