Building Construction
ይሓ ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበር በሚዛኒን ወለል የደረጃ መወጣጫ (BRIDGE) ለማሰራት ተጠንቶ በቀረበው ዝርዝር ስራዎችና ማቴሪያል መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Description
ቁጥር ይሓ/15764/19
ይሓ ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበር በሚዛኒን ወለል የደረጃ መወጣጫ (BRIDGE) ለማሰራት ተጠንቶ በቀረበው ዝርዝር ስራዎችና ማተሪያል መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል። ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት ያላችሁ ተጫራቾች GC 4 እና ከዚያ በላይ ፍቃድ ያላችሁ ጨረታው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ5 አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
በዚሁ መሰረት፦
1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 /ሶስት መቶ/ በመክፈል ከፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቁጥር 07 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
2. ተጫራች የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥርና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት ኮፒ ማቅረብ ይኖርበታል።
3. ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ብር 50,000 ሀምሳ ሺ ብር) በይሓ ሪል እስቴት ኃላ/የተ/የግ/ምህበር ሥም ሲፒኦ (CPO) በማሰራት ማስያዝ ይኖርበታል።
4. ተጫራች ከዚህ በፊት በጨረታ የተሳተፈባቸው ድርጅቶች መ/ቤቶች የመልካም የሥራ አፈፃፀም ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል።
5. ተጫራች የሚያቀርበውን የጨረታ ሰነዱ ቴክኒካል ለየብቻ ለይቶ በማሸግና በኢንቨሎፑ ላይ የተጫራች ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ለየብቻ ለይቶ በማሸግና በኢንቭሎፑ ላይ የተጫራች ማንነት በመግለፅ ክብ ማህተም በማድረግ ማቅረብ ይኖርበታል
6. ተጫራች ከላይ የተጠቀሱት መስፈርቶች ካላሟላ ከጨረታው የሚሰረዝ ይሆናል።
7. በጨረታ ማስታወቂያ እና ዶክመንቱ ላይ የተገለፁትን የመወዳደሪያ ነጥቦቹን ያሟሉ ተጫራቾች ብቻ ወደ ፋይናንሻል ግምገማ ያልፋል።
8. ጨረታው የሚዘጋበት ቀንና ሰዓት በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ 6 /በስድስተኛው የሥራ ቀን/ በስራ ሰዓት ከረፋዱ 2፡00 ስዓት ይሆናል።
9. ጨረታው የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ 6 በስድስተኛው የሥራ ቀን በስራ ሰዓት ከረፋዱ 2፡30 ሰዓት ይሆናል።
10. ተጫራች በጨረታው አሸናፊ መሆኑ ከተነገረበት ቀን ጀምሮ በሶስት የስራ ቀናት ውስጥ ከጠቅላ ዋጋ 10% ፐርፎርማንስ ቦንድ በማስያዝ 2ኛ ፎቅ ሰው ሃይል አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 12 በመቅረብ ውል ማሰር ይኖርበታል።
11. ተጫራች በጨረታው አሸናፊ መሆኑ ከተነገረበት ቀን ጀምሮ በሶስት የስራ ቀናት ውስጥ ከጠቅላ ዋጋ 10% ፐርፎርማንስ ቦንድ አስይዞ 2ኛ ፎቅ ሰው ሃይል አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 12 በመቅረብ ውል ተዋውሎ ወደ ስራው ካልገባ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ብር 50,000 ወደ ይሓ ሪል እስቴት ኃላ/የተ/የግ/ምህበር ሒሳብ ቁጥር ገቢ ይሆናል።
12. ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሉ መገኘት ይችላሉ።
አድራሻ፡- አዲስ አበባ ስቴድየም ቤተ ዛታ ሆስፒታል ፊት ለፊት “ይሓ ሲቲ ሴንተር ህንጻ 2ኛ ፎቅ ስልክ ቁጥር-
የቢሮ 011 55 8012 /011 557 6954/ ሞባይል - 09 22 07 95 75
ማሳሰቢያ፡- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
Tender details
- Deadline: 2026-10-13
- Bid closing time: 08:00
- Bid closing (note): ጨረታው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ 6 /በስድስተኛው የሥራ ቀን/ በስራ ሰዓት ከረፋዱ 2፡00 ስዓት
- Bid opening: 2026-10-13 08:30
- Bid opening (note): ጨረታው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ 6 /በስድስተኛው የሥራ ቀን/ በስራ ሰዓት ከረፋዱ 2፡30 ስዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Yiha Real Estate P.L.C.
- Buyer address: ይሓ ሲቲ ሴንተር ህንፃ
- Bid bond: 50,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Reporter (Oct 07, 2026)
- Posted at: 2026-10-08T12:50:09.000Z
- Source: Qelal Tenders