Audio Visual, Photography and Filming Service and Equipment

ሁንዴ ኦሮሞ ግራስሩትስ ዴቨሎፕመንት ኢኒሼቲቭ በቦረና ዞን በሚያከናውናቸው የሰብዓዊ ድጋፍ፣ የኑሮ ማሻሻያ፣ የአየር ንብረት መቋቋም አቅም ግንባታ፣ የተፈጥሮ ሀብት አስተዳደርና የማህበረሰብ ልማት ፕሮጀክቶች፡ የፕሮጀክት ሥራዎችን፣ ውጤቶችን፣ የማህበረሰብ ልምዶችንና የስኬት ታሪኮችን በሙያዊ መልኩ ለመመዝገብና ለማሰራጨት የዶክመንቴሽን፣ የቪዲዮ፣ የፎቶግራፍ፣ የኦዲዮ/ፖድካስት፣ የህትመት፣ የዲጂታል ይዘት

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ድርጅታችን ሁንዴ ኦሮሞ ግራስሩትስ ዴቨሎፕመንት ኢኒሼቲቭ በቦረና ዞን በሚያከናውናቸው የሰብዓዊ ድጋፍ፣ የኑሮ ማሻሻያ፣ የአየር ንብረት መቋቋም አቅም ግንባታ፣ የተፈጥሮ ሀብት አስተዳደርና የማህበረሰብ ልማት ፕሮጀክቶች፡ የፕሮጀክት ሥራዎችን፣ ውጤቶችን፣ የማህበረሰብ ልምዶችንና የስኬት ታሪኮችን በሙያዊ መልኩ ለመመዝገብና ለማሰራጨት የዶክመንቴሽን፣ የቪዲዮ፣ የፎቶግራፍ፣ የኦዲዮ/ፖድካስት፣ የህትመትና የዲጂታል ይዘት የማዘጋጀት አገልግሎት ከዚህ በታች ባለው መሠረት በጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል።

የጨረታው የአገልግሎት ዝርዝር

1. የፕሮጀክት ዶክመንቴሽንና የዶክመንተሪ ቪዲዮ ፕሮዳክሽን

2. የፎቶግራፍ፣ ኦዲዮ/ፖድካስት እና የስኬት ታሪኮች ዶክመንቴሽን

3. የህትመት፣ የዲጂታል ይዘት እና የድረ-ገጽ ላይ እንዲወጣ ማመቻቸት

የአገልግሎቱ ዝርዝር መግለጫ፣ መጠንና የሚፈለጉ ውጤቶች በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በዝርዝር የተገለጹ ሲሆን፣ ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ መሠረት የቴክኒክና የፋይናንስ ፕሮፖዛል ማቅረብ አለባቸው። የዶክመንቴሽን ሥራው በዋናነት የሚመለከታቸው አራት የHUNDEE ፕሮጀክቶች ሲሆኑ፣ እነሱም Multi-YeqrPro†racted CrisisEthiopia Joint Responses (2024–2026) እና Drought Anticipatory Action Strengthening Community-Led Seed System Initiative through Integrated Watershed Management Drought Recovery, Rehabilitation and Consolidation of Resilience Building እርና SI AGER - Sustainable Food Security and Resilience Building ናቸው፡፡

ስለሆነም በዚህ ዓይነት የዶክመንቴሽን፣ የቪዲዮ ፕሮዳክሽን፣ የፎቶግራፍ፣ የኦዲዮ/ፖድካስት እና የህትመት ሥራ ላይ ልምድ ያላቸው፣ የታደሰና ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው እና በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች የጨረታ ሰነዱን 300.00 ብር በመክፈል ከድርጅቱ መግዛት ይችላሉ። (የጨረታ ሰነዱ በሶፍት ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 3% የሚሆን የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) በሁንዴ ኦሮሞ ግራስሩትስ ዴቨሎፕመንት ኢኒሼቲቭ ስም በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ/የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው። የBid Bond ከጨረታ ዋጋ ማቅረቢያው ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ ተካትቶ መቅረብ ይኖርበታል።

የጨረታ ሰነዱን መግዛትና የጨረታ ሰነዱን ማቅረብ የሚቻለው የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ9 ተከታታይ የሥራ ቀናት ሲሆን፣ በአዲስ አበባ፣ መስቀል ፍላወር አደባባይ አካባቢ፣ ከቪላ ቨርዴ ሆቴል አጠገብ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ማቅረብ ይችላሉ።

የጨረታ ሰነዱ የሚቀርበው ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በዘጠነኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ የሚዘጋ ሲሆን፣ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡20 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱን የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፦

ስልክ፦ 011 558 3967 / 011 558 2328 / 09 13 39 98 17

ሁንዴ ኦሮሞ ግራስሩትስ ዴቨሎፕመንት ኢኒሼቲቭ


Tender details

  • Deadline: 2026-10-16
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በዘጠነኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-16 10:20
  • Bid opening (note): ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በዘጠነኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡20 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Hundee Oromo Grassroots Development Initiative
  • Bid bond: 3%
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Reporter (Oct 07, 2026)
  • Posted at: 2026-10-08T14:53:10.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders