Building Construction

በኦሮሚያ ክልል መስተዳደር በደቡብ መዕራብ ኦሮሚያ ዞን ሠኮሩ ወረዳ መንገዶችና ሎጅስቲክስ ጽ/ቤት በ2019 ዓ.ም በጀት ገጠር መንገድ ግንባታና ጥገና በሙሉ ውል(Full Contract) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል

Description

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ክልል መስተዳደር በደቡብ መዕራብ ኦሮሚያ ዞን ሠኮሩ ወረዳ መንገዶችና ሎጅስቲክስ ጽ/ቤት በ2019 ዓ.ም በጀት ገጠር መንገድ ግንባታና ጥገና በሙሉ ውል(Full Contract) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

የሥራ ዓይነት

  • የገጠር መንገድ ጥገና፦ ከደነባ – ጫላ = 8ኪሜ
  • ገጠር መንገድ ግንባታ፦ 1, ሰቀልጋ - ኮሚነ = 5ኪሜ 2, በቁምቢ ከተማ ውስጥ = 3ኪሜ

ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው፡-

  1. የ2018 ዓ.ም የመንግስት ግብር የከፈሉ፣ አመልካቾች ህጋዊ የመንገድ ግንባታ ፍቃድ(PPC) ያላቸው ወይም አጠቃላይ የግንባታ ሥራ ተቋራጭ(GC) ፍቃድ ያላቸው እና የ 2019 ዓ.ም ንግድ ፍቃድ ያሳደሱ መሆን አለበት።
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ(VAT) ተመዝጋቢ እና ቲን ቁጥር(TIN) ሊኖረው ይገባል።
  3. TOT (3%) ለመክፈል ፈቃደኛ መሆን አለበት።
  4. አስፈላጊውን ባለ ሞያ፣ የሰው ሃይል፣ ማሽነሪ እና መሳሪያዎች በህጋዊ መንገድ ማግኘት ወይም ያለው መሆን አለበት።
  5. በጨረታ ሰነዶች ውስጥ የተቀመጡትን ሁሉንም መስፈርቶች ማሟላት አለበት።
  6. ተወዳዳሪው ከዚህ ብፊት የሰራውን ስራ በጥራት እና ያለምንም ችግር እንዳከናወነ የሚገልጽ የጥራት እና የልምድ የምስክር ወረቀት ከተለያዩ የሰራባቸው ቦታዎች ማቅረብ አለበት።
  7. ከማንኛውም የመንግስት ግዥ ዕገዳ ነፃ መሆኑን ከፌዴራል የግዥ እና የንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ በተሰጠው የተረጋገጠ መሆን አለበት።
  8. ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ CPO ወይም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ 300,000.ETB በአንድ ፖስታ ለብቻው ታሽጎ ከዋናው ሰነድ ጋር አንድ ላይ ታሽጎ ማቅረብ አለባቸው።
  9. በተሰጠው ዲዛይን መሠረት መስራት የሚችል።
  10. አሸናፊው አስፈላጊውን መስፈርት ያሟላ እና በእያንዳንዱ መስመር ላይ ቫትን ጨምሮ ዝቅተኛ ዋጋ ባቀረበው ላይ ተጫራቹ አሸናፊ ይሆናል።
  11. የጨረታ ሰነዱ ስረዘ፣ ድልዝ ወይም የተሳሳተ ከሆነ ተቀባይነት አይኖረውም።
  12. አሸናፊው ተጫራች ለስራው ውል ለመፈፀም በተባለው ቀን ውስጥ ካልቀረበ ተጫራቹ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ተደርጎ ተጫራቹም በህግ ተጠያቂ ይሆናል።
  13. የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ሁለት ሺህ (2000) ብር ሠኮሩ ወረዳ በገቢዎች ጽ/ቤት በመክፈል ደረሰኝ በመያዝ ከገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር.5 በመቅረብ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15(አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት መግዛት ይችላሉ።
  14. የጨረታው ሰነድ ቴክኒካል ኦርጅናል እና ፋይናንሻል ኦርጅናል አንድ(1) እና ፎቶ ኮፒ ሁለት(2) ለእያንዳንዱ መንገድ(For Each Lots) አንድ በአንድ ለየብቻ በማድረግ በተለያየ ፖስታ በማሸግ “ቴክኒካል ኦርጅናል”፣ “ፍእይናንሽእል ኦርጅናል”፣ “ቴክኒካል ኮፒ 2”፣ “ቴክኒካል ኮፒ 2”፣ “ፋይናንሻል ኮፒ 1” እና “ፋይናንሻል ኮፒ 2” በማለት ላዩ ላይ በመፃፍ በሁሉም ፖስታ ላይ የሁሉንም መስመሮችን ስም ፣ የባለቤቱን ወይም የድርጅቱን ስም፣ አድራሻ እና ስልክ ቁጥር እንደዚሁም የመንገድ ጫረታው የወጣበት ቁጥር ላዩላይ በመፃፍ በድርጅቱ መሃተብ ላዩላይ ተመቶ በታሸገ ኤንቨሎፕ ሁሉም በአንድ ፖስታ ታሽጎ መቅረብ አለበት።
  15. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሚመለከታቸው የመንግስት የግዥ ህጎች እና ደንቦች እና የጨረታ ሰነዶች መሰረት የጨረታውን ሂደት የመቀበል፣ የመሰረዝ ወይም የማስተካከል መብቱ የተጠበቀ ነው።
  16. የጨረታው ሳጥን በ ቀን 19/02/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግተው በዚያው ቀን 19/02/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቻው በተገኙበት ይከፈታል።

ለበለጠ መረጃ :- በስልክ ቁጥር 09 30 40 50 12 ወይም 09 35 15 20 72 ደውሎው መጠየቅ ይችላሉ።
በኦሮሚያ ክልል መስተዳደር በደቡብ መዕራብ ኦሮሚያ ዞን ሠኮሩ ወረዳ መንገዶችና ሎጅስቲክስ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-29
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-10-29 10:30
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Skoru woreda Road Authority
  • Bid bond: 300,000.00 (ሶስት መቶ ሺህ ብር)
  • Bid document price: 2000.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 09, 2026)
  • Posted at: 2026-10-09T09:04:06.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders