Land Lease & Real Estate

የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር መሬት መምሪያ ለመኖሪያ አገልግሎት 130 እና የንግድ 15 ቦታዎች በድምሩ 145 ቦታዎችን በጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል

Description

የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 መሰረት በ2019 በጀት ዓመት 1ኛ ዙር መደበኛ የሊዝ ጨረታ ለመኖሪያ አገልግሎት 130 እና የንግድ 15 ቦታዎች በድምሩ 145 ቦታዎችን በጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል።

በመሆኑም፡-

መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ/ድርጅት/ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጨረታው እንደሚጀምር ከተነገረበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 1,000 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል ቀበሌ 08 ከአዲሱ መሬት መምሪያ ቢሮ ቢሮ ቁጥር 310 በመምጣት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላል።

የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ በማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ምሽቱ 11፡00 ሰዓት ብቻ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በቢሮ ቁጥር 310 ይሆናል።

ጨረታው የሚዘጋው በ10ኛው ቀን ከቀነ በ11፡00 ሰዓት ይሆናል።

ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው ከተዘጋበት ቀን ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ጀምሮ ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሲሆን ጨረታው የሚከፈትበትን ቦታ በተመለከተ በውስጥ ማስታወቂያ የሚገለጽ ይሆናል።

ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ በመምሪያው የውስጥ ማስታወቂያ መለጠፊያ ሰሌዳ እና በBahirdar City Communication የፌስ ቡክ ገፅ ማግኘት ይቻላል።

መስሪያ ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር መሬት መምሪያ


Tender details

  • Deadline: 2026-10-21
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): በማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከቀኑ በ11፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-22 10:00
  • Bid opening (note): ጨረታው ከተዘጋበት ቀን ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር መሬት መምሪያ
  • Bid document price: 1000 (አንድ ሺህ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Oct 10, 2026)
  • Posted at: 2026-10-10T08:06:59.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders