Construction Machinery
የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ለ2019 ዓ.ም. የበጀት ዓመት በክልሉ ውስጥ ለመንገድ ጥገና እና ግንባታ ስራ የሚያገለግሉ የተለያዩ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪዎችን በጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል
Description
ግልጽ ብሄራዊ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 03/2019 ዓ/ም
የማሽነሪ እና ተሸከርካሪ ኪራይ አገልግሎት ግዥ
የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ለ2019 ዓ.ም የበጀት ዓመት በክልሉ ውስጥ ለመንገድ ጥገና እና ግንባታ ስራ የሚያገለግሉ የተለያዩ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪዎችን በጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈለጋል።
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች መሠረት በማድረግ በጨረታዉ እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የጸና ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፤
- ተጫራቾች የሚጠበቅባቸውን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፣
- የግዥውመጠን ብር 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ NAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- በኪራይ የሚቀርቡት ተሽከርካሪዎች እና ማሽነሪዎች የፈረስ ጉልበታቸው፣ የስሪት ዘመናቸውና ሌሎች ከጨረታ ሰነዱ የተገለፁት መስፈርቶች ተሟልተው መቅረብ አለባቸው።
- በኪራይ የሚቀርቡ ተሽከርካሪና ማሽነሪዎች ኪሎ ሜትር ወይም የነዳጅ ቆጣሪው በትክክል የሚሰራ መሆን አለበት።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለማሽነሪዎች የጠቅላላ ዋጋዉን 1% ሆኖ ለሌሎች ተሽከርካሪዎች ለእያንዳንዱ ብር 10,000.00 በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ብሄራዊ ባንክ እውቅና ከሰጣቸው ባንኮች ብቻ ማስያዝ አለባቸዉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ ብቻ በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ስም በተከፈተው በኢትዮጵያ ንገድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000013197966 ገቢ በማድረግ የባንክ ዲፖዚት ስሊፕ ኮፒውን በመያዝ ከገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 09 ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ከ30/-01-/2019 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 10-/02-/2019 ዓ.ም ዋናው መ/ቤት ባህር ዳር በአካል በመገኘት መግዛት ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱን ፋይናንሻሉንና ቴክኒካል በፖስታ በማሸግ የተሟላ አድራሻ በመፃፍ በሁለት ፓስታ ኦርጅናልና ኮፒ ተብሎ ተዘጋጅቶ ከግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ ቁጥር 03 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 10/02/2019 ዓ.ም 8፡00 ስዓት ድረስ በአካል በመገኘት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኤጄንሲው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ወይም ከግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ ቁጥር 03 በ-10/-02/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በ8፡30 ስዓት ይከፈታል። እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት ይከፈታል።
- የዋጋ መሙያቅፁ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለው ከጨረታውውድድር ውጭ ይደረጋል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058-320-55-55 ወይም 058-222-11-07 በመደወል ወይም በኤጀንሲው ደህረ ገጽ www.arrca.gov.et ማግኘት ይችላሉ።
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጄንሲ
Tender details
- Deadline: 2026-10-20
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-10-20 14:30
- Region: Amhara
- Publishing entity: Amhara Rural Roads Construction Agency
- Bid bond: ለማሽነሪዎች የጠቅላላ ዋጋዉን 1% ሆኖ ለሌሎች ተሽከርካሪዎች ለእያንዳንዱ ብር 10,000.00
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Oct 10, 2026)
- Posted at: 2026-10-10T08:17:12.000Z
- Source: Qelal Tenders