Construction Machinery and Equipment

በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ የኤክስካቫተር ኪራይ አገልግሎት ግዥ እና የሎደር ኪራይ አገልግሎት መግዛት ይፈልጋል

Description

በድጋሚ የወጣ የኤክስካቫተርና የሎደር ኪራይ

አገልግሎት ግዥ ብሔራዊ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡- አግጨ /0011/ኦኩስፋ-2/2018 ዓ.ም

1.በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ በድጋሚ የወጣ

  • ሎት 1 የኤክስካቫተር ኪራይ አገልግሎ ግዥ
  • ሎት 2 የሎደር ኪራይ አገልግሎት መግዛት ይፈልጋል።

2. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ /CPO/ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የ120 ቀን የባንክ ዋስትና //BIDBOND / በመስኩ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ ተጫራቾች በመንግስት ግዥ የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር/supplier List ውስጥ መካተታቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና በተጨማሪ የበጀት ዓመቱን ታክስ ክሊራንስ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።

3.ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ቀን ውሎ በአስራ ስድስተኛ ቀን ይከፈታል። የጨረታውን መክፈቻ ትክክለኛ ቀን በጨረታ ሰነዱ ላይ በግልጽ ተቀምጧል፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል።

4.ብቁ ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ ለሁሉም የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ ከሰዓት በፊት ከ2፡00-6፡00፣ ከሰዓት በኃላ ከ7፡00-10፡30 እና ቅዳሜ ከሰዓት በፊት ከ2፡00-6፡00) ቀጥሎ በተመለከተው አድራሻ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

5.የጨረታው ሰነድ የሚሸጥበት ለውድድር የቀረበ ሰነድ የሚገባበትና የሚከፈትበት አድራሻ ቀጥሎ በተጠቀሰው ነው።

5.1. አሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ የስኳር ፋብሪካዎች ማስተባበሪያ ቢሮ ቶታል ሶስት ቁጥር ማዞሪያ 300 ሜትር ከፍ ብሎ ተዘነኦ ሆስፒታል አጠገብ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ግቢ ውስጥ።

ስልክ ቁጥር፡ 09-91-14-94-85/0986862766/ 0940209464

አዲስ አበባ/ ኢትዮጵያ

6. ተጫራቾች ለሁለቱም ሎቶች አንድ ላይ ጨረታ የማስከበሪያ ዋስትና ብር 60,000 (ስልሳ ሺህ ብር) በሲ.ፒ.ኦ ወይም በባንክ የተረጋገጠ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።

7. የዕቃው ርክክብ የሚፈፀመው ኦሞ ኩራዝ ቁጥር ሁለት ስኳር ፋብሪካ የሚገኝበት ደቡብ ኦሞ ዞን ኃይል ውሃ ቀበሌ ነው።

8.ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ30 ቀናት ነው።

9.የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ የመቆያ ጊዜ የጨረታው ዋጋ ፀንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ለ28 ቀናት ነው።

10.ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ኦሞ ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ

Tel- 0940209464

ኃይል ውሃ

አዲስ አበባ ግዥ ማስተባበሪያ ቢሮ

Tel: 09-91-14-94-85/0986862766

አዲስ አበባ

ኦሞ ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ


Tender details

  • Deadline: 2026-10-26
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ቀን
  • Bid opening: 2026-10-27 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ቀን ውሎ በአስራ ስድስተኛ ቀን
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Omo Kuraz No-2 Sugar Factory
  • Bid bond: 60,000.00 (ስልሳ ሺህ ብር)
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Oct 11, 2026)
  • Posted at: 2026-10-12T07:27:44.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders