Distribution of Different products

ኬኛ ቢቨሬጅስ አ.ማ. የምርቶች አከፋፋይነት ፍላጎት መግለጫ ጥሪ

Description

ኬኛ ቢቨሬጅስ አ.ማ.
የምርቶች አከፋፋይነት ፍላጎት መግለጫ ጥሪ

1.መግቢያ

ከ5,000 በላይ የሆኑ የአክሲዮን ባለቤቶች በሚያዝያ 2009 ዓ.ም. ኬኛ ቢቨሬጅስ አ.ማ.ን መሰረቱ᎓᎓ ድርጅቱ በኦሮሚያ ክልል፣ በምዕራብ ሸዋ ዞን፣ በጊንጪ ከተማ አቅራቢያ የሚገኝ ሲሆን፣ ዘመናዊና ከፍተኛ ቴክኖሎጂ የሚጠቀም 3 ሚሊዮን ዘ የማምረት አቅም ያለው የመጠጥ ፋብሪካ ሲሆን፣ አቅሙን ወደ 6 ሚሊዮን ዜ ለማሳደግ በሚያስችለው መልኩ እየሰራ ይገኛል።

ድርጅቱ አልኮል ያላቸውንና ከአልኮል ነፃ የመጠጥ ምርቶችን በከፍተኛ ጥራት እያመረተ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም፣ በሁለተኛው የሥራ ምዕራፍ እንደ ጭማቂ፣ ካርቦኔትድ ውሃ እና ሌሎች የምርት ዓይነቶችን ለመጨመር አቅዷል።

2. የፍላጎት መግለጫ የሚቀርብበት ይዘት

አመልካቾች የኬኛ ቢቨሬጅስ አማ. አከፋፋይ ሆነው ለመስራት ያላቸውን ፍላጎትና ብቃት በግልጽ የሚገልጽ የፍላጎት መግለጫ ማቅረብ አለባቸው፡፡ የሚቀርበው የፍላጎት መግለጫ ቢያንስ የሚከተሉትን ጉዳዮች ማካተት አለበት:

  • የገንዘብ አቅም
  • የገበያ ሽፋን አቅም
  • የመጋዘንና የአከፋፋይነት አቅም
  • የሕግና የተገዢነት መስፈርቶች

3. የብቃት መመዘኛ መስፈርቶች

የቀረቡ ማመልከቻዎች በሚከተሉት የግምገማ መስፈርቶች እና ለእያንዳንዱ መስፈርት በተመደበው ክብደት መሠረት ይገመገማሉ፦

የግምገማ መስፈርት

ክብደት (%)

የፋይናንስ አቅም

20%

የአሠራር አቅም: መጋዘን፣ ተሽከርካሪዎች፣ የሰው ኃይል እና ቴክኖሎጂ

20%

የንግድና የሽያጭ አቅም

20%

የገበያ ሽፋን አቅም

15%

ድርጅታዊ መዋቅርና አስተዳደር

10%

ሕግ፣ ተገዢነት እና የንግድ ተዓማኒነት

10%

ስትራቴጂያዊ ተጣጣሚነት

5%

ድምር

100%

  • መጋዘን: መጋዘኑ ጠንካራና ለረጅም ጊዜ ሊያገለግሉ ከሚችሉ ቁሳቁሶች የተገነባ፣ ከፍተኛ ክብደትንና ተደጋጋሚ የሥራ እንቅስቃሴን መቋቋም የሚችል፣ እንዲሁም የምርቶችን ጥራትና የምግብ ደህንነት መስፈርቶችን ሙሉ በሙሉ የሚያሟላ መሆን አለበት፡፡ የመጋዘኑ ስፋት ከ250 ካሬ ሜትር (250 m2) በታች መሆን የለበትም።
  • ተሽከርካሪዎች: ምርቶችን ከኬኛ ቢቨሬጅስ አ.ማ. ፋብሪካ ወደ አከፋፋይ መጋዘን ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ የመጀመሪያ ደረጃ የሽያጭ ተሽከርካሪዎች ፡ እንዲሁም ምርቶችን በተመደበው የአከፋፋይ አካባቢ ውስጥ ወደሚገኙ የሽያጭ ቦታዎች ለማድረስ የሚያገለግሉ የሁለተኛ ደረጃ የሽያጭ ተሽከርካሪዎችን ማዘጋጀት ይኖርባቸዋል።

የሰው ኃይል መስፈርቶች: የሽያጭና የአከፋፋይነት ሥራዎች በብቃት እንዲከናወኑ፣ ሁሉም የኬኛ ቢቨሬጅስ አ.ማ. አከፋፋዮች ቢያንስ የሚከተሉትን ሠራተኞች ለዚህ ሥራ መመደብና በሕጋዊ የሥራ ውል መሠረት ማሟላት አለባቸው፦

  • የሽያጭ/የስርጭት ተቆጣጣ
  • የሽያጭ ሰራትኞች
  • የስርጭት መኪና አሽከርካሪዎች
  • ጫኚዎች/አውራጆች እና የመጋዘን ረዳቶች

የአከፋፋይነት ልምድ: አመልካች ድርጅቶች ፈጣን የሸማች ምርቶችን (MCG) በአከፋፋይነት ሥራ ረገድ ልምድ ያላቸው ቢሆኑ ይመረጣል፡፡ በተጨማሪም፣ የአካባቢውን ቋንቋና ባህል መረዳት እንደ ተጨማሪ ጥቅም ይታያል፡

የጥቅም ግጭት: አመልካቾች ከኬኛ ቢቨሬጅስ አ.ማ. ሠራተኛ ወይም የሠራተኛ ቤተሰብ አባል በአመልካች ድርጅቱ ውስጥ የባለቤትነት፣ የአስተዳደር ወይም የፋይናንስ ጥቅም ካለው በግልጽ መግለጽ አለባቸው፡፡ ማንኛውም ያልተገለጸ ግንኙነት ወይም የጥቅም ግጭት ካለ፣ ማመልከቻው ተቀባይነት አያገኝም።

የኬኛ ቢቨሬጅስ አ.ማ. ምርቶችን ለማከፋፈል የአከፋፋይነት መብት ከመስጠቱ በፊት፣ እጩ አመልካቾች ላይ በቂ የማጣራት ሂደት ያከናውናል፡፡ ይህ ሂደት የመጋዘን፣ የተሽከርካሪዎችና የቢሮ ማረጋገጫ፣ የገንዘብ አቅም ግምገማ፣ የሕግ፣ የንግድና የግብር መስፈርቶችን ማክበር ማረጋገጥ፣ እንዲሁም የማጣቀሻ እና የልምድ ማረጋገጫ ያካትታል።

የዚህ ማጣራት ውጤት በመደበኛ የግምገማ ውጤት ሰንጠረዥ ላይ ተሰብስቦ ይገመገማል። የአከፋፋይ ምደባውም የኬኛ ቢቨሬጅስ አ.ማ.ን የውስጥ ሂደት በመከተል፣ ተረጋግጦና ጸድቆ ይከናወናል።

የአከፋፋዮች ምደባ ሁኔታ

የተመረጡ አከፋፋዮች የኬኛ ቢቨሬጅስ አ.ማ. ምርቶች የአከፋፋይነት ስምምነት መፈራረም አለባቸው፡፡ እንዲሁም የተመላሽ ሳጥንኖችን ዋጋን እና ሊሰጥ የሚችል ማንኛውንም የንግድ ብድር ለመሸፈን፣ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የሚፈጸም የባንክ ዋስትና ወይም የገንዘብ ማስያዣ አንዳስፈላጊነቱ ማቅረብ አለባቸው። ቼክ እንደ ዋስትና አይቀበልም።

አዲስ አከፋፋዮች በመጀመሪያ ምርቶችን በጥሬ ገንዘብ በመግዛት የንግድ ሥራቸውን ይጀምራሉ፡፡ ከተመደቡ በኋላ፣ በግምገማ ውጤታቸውና በአከፋፋይነት ታሪካቸው ላይ በመመሥረት፣ በኬኛ ቢቨሬጅስ አ.ማ. ፖሊሲና መመሪያ መሠረት የንግድ ብድር ሊሰጣቸው ይችላል።

የኬኛ ቢቨሬጅስ አ.ማ. ምርቶችን የሚያከፋፍሉ አከፋፋዮች የአከፋፋይ ምደባ ሂደታቸው ሙሉ በሙሉ ከተጠናቀቀ በኋላ ብቻ የምርቶቹን ንግድ መጀመር ይችላሉ። ይህም ስምምነት መፈራረም፣ አስፈላጊውን የድርጅት ሥርዓት ማዘጋጀትና ማጽደቅ፣ እንዲሁም የአከፋፋይ አካባቢና የምርት ዋጋ መመደብ/ማሳወቅን ያካትታል።

4. የማመልከቻ ማቅረቢያ መስፈርቶች

ፍላጎት ያላቸው አመልካቾች ከማመልከቻቸው ጋር የሚከተሉትን አስፈላጊ ሰነዶች ማቅረብ አለባቸው፦

  • የንግድ ፈቃድ፣ የVAT ምዝገባ ማረጋገጫ እና የTIN ማረጋገጫ ቅጂዎች።
  • አመልካቾች በኬኛ ቢቨሬጅስ አ.ማ. የተቀመጡትን የገንዘብ አቅም መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፡፡ ይህም ቢያንስ የተጣራ ሀብት/ የተከፈለ ካፒታል እና ባለፉት ሦስት (3) ዓመታት ውስጥ የተገኘ ዝቅተኛ አማካይ ዓመታዊ የሽያጭ ገቢ ያካትታል፡፡ እነዚህ መስፈርቶች በኦዲት በተደረጉ የፋይናንስ መግለጫዎች እና የግብር ክሊራንስ መረጋገጥ አለባቸው።
  • የባንክ መግለጫዎች፣ የባለፉት ሦስት (3) ዓመታት የባንክ መግለጫዎች።
  • የሥራ ዓይነት፣ የድርጅቱን ታሪክ፣ የአገልግሎት ጥራትና የድርጅቱን አቅም በግልጽ የሚያብራራ።
  • የተሽከርካሪዎችንና የመጋዘን ቦታዎችን ባለቤትነት ወይም ኪራይ የሚያረጋግጡ ሰነዶች።
  • በተመደበው የአከፋፋይ አካባቢ ላይ ያላቸውን ፍላጎትና አቅም የሚገልጽ ደብዳቤ።

ፍላጎት ያላቸውና ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አመልካቾች፣ የፍላጎት መግለጫ እና አስፈላጊዎቹን ሰነዶች ቅጂ በማድረግ፣ በኤሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል፣ አዲሱ ሕንፃ፣ 13ኛ ፎቅ በሚገኘው የኬኛ ቢቨሬጅስ አማ. ዋና መሥሪያ ቤት፣ ከጥቅምት 20፣ 2019 ዓ.ም. በፊት በአካል በመቅረብ በተዘጋጀላቸው ሳጥን ውስጥ በማስገባት በተጠቀሰው ወቅት ስለማስገባታቸው የተዘጋጀውን ፎርም መፈረም አለባችው።

የሚቀርበው ማመልከቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ መቅረብ አለበት:: ኤንቨሎፑ የአመልካች ድርጅቱን ስም እና የማመልከቻውን ርዕስ በግልጽ ሁኔታ ማሳየት አለበት። ለምሳሌ፦ “የኬኛ ቢቨሬጅስ አ.ማ. ምርቶች አከፋፋይነት የፍላጎት መግለጫ”

5. የሕግ ማስታወሻ

  • ይህ ማስታወቂያ በኬኛ ቢቨሬጅስ አ.ማ. ላይ ማንኛውንም የውል ወይም የሕግ ግዴታ አይፈጥርም።
  • ኬኛ ቢቨሬጅስ አ.ማ. ይህንን ማስታወቂያ በሙሉ ወይም በከፊል የማሻሻል፣ የመቀየር ወይም የመሰረዝ፣ እንዲሁም በማመልከቻ ወይም በአከፋፋይ ምደባ ሂደቱ ላይ አስፈላጊ ለሆነ ለውጥ የማድረግ ሙሉ መብት አለው፡።
  • በተወሰነው ጊዜ ውስጥ ያልቀረበ ማንኛውም ማመልከቻ ተቀባይነት አይኖረውም።
  • በማጣራት የተመረጡና ወደ ቀጣዩ የምርጫ ሂደት ያለፉ አመልካቾች፣ የኬኛ ቢቨሬጅስ በሚመድባቸው ሰራተኞች የመስክ ጉብኝት የሚያደርጉ ሲሆነ ለአመልካቾች ተዘጋጅተው አነዲጠብቁ በቅድሚያ ይነገራቸዋል ።

6. የአከፋፋይ አካባቢዎች

ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት የአከፋፋይ አካባቢዎች አመልካቾች ይጋበዛሉ፦

1. አዲስ አበባ

8. ቡታጅራ

15. መቱ-1

2. አዶላ

9. ደምቢ ዶሎ

16. ሞጆ

3. አሰላ

10. ዲላ

17. ሶዶ

4. ቢሾፍቱ

11. ሆሳዕና

18. ሱሉልታ

5.ቦንጋ

12. ሆለታ

19. ወልቂጤ

6. ቡሌ ሆራ

13. ጅማ

 

7. ቡራዩ

14. መቻራ

 

ይህ ጥሪ ፍላጎት ላላቸው ሁሉም አካላት ክፍት ነው። ሆኖም፣ ኬኛ ቢቨሬጅስ አ.ማ. የድርጅቱን የንግድ ፍላጎቶች የሚያሟሉ አመልካቾችን የመምረጥ ሙሉ መብት አለው።

ኬኛ ቢቨሬጅስ አ.ማ. የፍላጎት መግለጫችሁን ለመቀበል እና ከተመረጡ አካላት ጋር የረጅም ጊዜ የንግድ አጋርነት ለመመስረት በጋራ ለመስራት በጉጉት ይጠብቃል።

ካዛንቺስ፣ ኤሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል፣ አዲሱ ሕንፃ፣ 13ኛ ፎቅ +251 9 28977983 www.kegnabeverages.com 


Tender details

  • Deadline: 2026-10-30
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid opening: 2026-10-30 17:00
  • Bid opening (note): የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰአት አልተገለፀም
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Kegna Beverages S.C.
  • Published on: Reporter (Oct 11, 2026)
  • Posted at: 2026-10-12T12:46:25.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders