Installation, Maintenance and Other Engineering Services
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለመሀል አምባ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አማካይነት ለሚያሰራው የሆስፒታሉ ሙሉ የኤሌትሪክ መስመር ዝርጋታ ስራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Installation, Maintenance and Other Engineering ServicesElectrical, Electromechanical and ElectronicsFinishig Works
Central Ethiopia
Description
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ
ማስታወቂያ መለያቁጥር GGWW/0004/2019
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለመሀል አምባ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አማካይነት ለሚያሰራው የሆስፒታሉ ሙሉ የኤሌትሪክ መስመር ዝርጋታ ስራ በግልጽ ጫረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች
- የዘመኑ ንግድ ፍቃድ ያሳደሱ የቫት እና ቲን ነምበር ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡
- የመወዳደሪያ ደረጃቸውም ደረጃ 8 እና ከዛ በላይ በኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ የሙያ ፍቃድ ያላቸው የሆኑ ተቋራጮች 2 ከገቢዎች መስሪያ ቤት የኦዲት ክሊራንስ ማምጣት የሚችሉ
- ተወዳዳሪዎች የቫት 7.5%ተቀናሽ ለማድረግ ፍቃደኛ መሆን አለባቸው
- በጨረታው ለመወዳዳር የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች የሚገዙት ጨረታ ሰነዱን ጠቅሰው በማመልከቻ ሲጠይቁ የድርጀቱ ባለቤት መሆን አለባቸው እንዲሁም በውክልና ሰነዱን መውሰድና መወዳደር አይቻልም፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው የስራ ቀናት እስከ 8፡00 ሰአት ድረስ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር ብቻ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መሀል አምባ ገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ 50000 /ሀምሳ ሺህ ብር/ በገ/ጉ/ወ/ወ/ፋይናንስ ፅ/ቤት ስም ማሰራት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶክመንት ሀ/ ለቴክኒካል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማድረግ ቴክኒካል በሚል በመለየት ለ/ለፋይናንሻል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማደረግ ፋይናንሻል በሚል በመለየት በሰም በማሸግ ከላይ በተጠቀሰው የጫረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከቴክኒካል ኦርጅናል ዶክመንቱ ጋር በማድረግ በሰም በማሸግ ቴክኒካል ዶክመንት በሚል በመለየት ይህማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10( አስር ) የስራ ቀናት መሀልአምባ የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮቁጥር 03 ድረስ በመምጣት ለጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው ሰነድ በ10ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይታሸጋል ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- መስሪያቤቱ የተሻለ መንገድ ከገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡-
- በአፈፃፀም ምክንያት ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ድርጅቶች መወዳደር አይችሉም፡፡
- ተጨራቾች ተጫርተው ካሸነፉ በኃላ አገልግሎታቸው ጥራት ያለውና ቀልጣፋ ካልሆነ የውል ጊዜን የምናቋርጥ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በአል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የስራ ቀን ይዘዋወራል፡፡
- ተውዳዳሪዎች ከአሸነፉ በኋላ ቅደመ ክፍያ ሳይጠይቁ ስራው መስራት የሚችሉ መሆን ፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ስልክ ቁጥር 011 336 0631/146 ይደውሉ
ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
መሀል አምባ
Tender details
- Deadline: 2026-10-22
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-22 14:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
- Region: Central Ethiopia
- Publishing entity: Gurage Zone Gedebano Gutazer Welene Woreda FEDB
- Bid bond: 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)
- Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Oct 12, 2026)
- Posted at: 2026-10-13T06:43:26.000Z
- Source: Qelal Tenders