Transportation Service
በጋሞ ዞን የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በጋሞ ዞን የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት የተለያዩ የግዥ አገልግሎቶችን
- ሎት 1 የአፈር ማዳበሪያ ከዞን ማዕከል ወደ ቀበሌያትና ከቀበለያት ወደ ቀበሌያት የማጓጓዣ አገልግሎት ግዥ፣
- ሎት-2 የሕንፃ መሳሪያዎች የፋብሪካ ውጤቶች ግዥ
- ሎት 3 የታሸገ የቆሎ ግዥ
- ሎት-4 የተለያዩ የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡
በዚሁ መሠረት በጨረታው መሳተፍ የሚትፈልጉ በዘርፉ የተሰማራችሁ ድርጅቶችና ግለሰቦች ለጨረታው ውድድር ማቅረብ ያለባችሁ መስፈርቶች የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ፣ የንግድ ስራ ምዝገባ ሰርትፊኬት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርትፊኬት፤የግብር መክፈያ ቁጥር የአቅራቢነት ሰርትፍኬትና የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት ለየብቻው ብር 20,000 /ሃያ ሺህ/ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ ክፍያ ማዘዣ CPO ከታወቀ ባንክ በማዘጋጀት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከመ/ቤቱ ግዥና ንብረት አስተዳዳር ዘወትር በስራ ሰዓት በመቅረብ የማይመለስ 100 /አንድ መቶ/ ብር በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ዋጋው ያለ ስርዝ ድልዝ በጥንቃቄ በመሙላት በሰነዱ ላይ ፊርማና ማህተም በማድረግ በፖስታ አሽጎ በፖስታው ላይም ማህተም የጨረታውን ዓይነት እና ስልክ በመጻፍ በዕለቱ ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 15 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ በዕለቱ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን ድንገት የሥራ ቀን ሳይሆን ቢቀር በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ሂደቱ ይከናወናል፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፤- ከመዲኃኒዓለም ቤተክርስቲያን ዝቅ ብሎ ወደ የትነበርሽ ማዞሪያ ላይ ባለው ዲንጉዛ ሕንፃ ውስጥ እንገኛለን፡፡
አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስና ኘላን ልማት
ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-30
- Bid closing time: 11:00
- Bid closing (note): በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 15 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-30 14:00
- Bid opening (note): በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 15 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 8፡00 ሰዓት
- Region: South Ethiopia Regional State
- Publishing entity: Gamo Zone Arba Minch Surrounding Woreda Finance and Economic Development Bureau
- Bid bond: ለእያንዳንዱ ሎት 20,000 (ሀያ ሺህ ብር)
- Bid document price: 100 (አንድ መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Oct 13, 2026)
- Posted at: 2026-10-13T08:19:35.000Z
- Source: Qelal Tenders