Construction Machinery and Equipment
የሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን ለ2019 በጀት ዓመት በክልሉ ውስጥ የመንገድ ግንባታ ሥራ ለማሠራት የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች መስፈርቱን ከሚያሟሉ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አውዳደሮ መከራየት ይፈልጋል
Description
ለመጀመሪያ ዙር የወጣ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር፡- ሲ/መ/ባ/002/2019
የማሽን ኪራይ አገልግሎት የግለጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን ለ2019 በጀት ዓመት በክልሉ ውስጥ የመንገድ ግንባታ ሥራ ለማሠራት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች መስፈርቱን ከሚያሟሉ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አውዳደሮ መከራየት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የማሽነሪ ዓይነት |
ብዛት |
የአንዱ ሰዓት |
ጠቅላላ ሰዓት |
|
1 |
ግሬደር |
5 |
850 |
4,250 |
|
2 |
ሮሌር |
5 |
850 |
4,250 |
በዚሁ መሠረት፡-
1.ተጫራቾች አግባብነት ያለውን ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ እንዲሁም የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸውን የሚያሳይ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2.ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ ቀናት ከባለሥልጣኑ መ/ቤት ግዥ የፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር -5 ቀርበው መግዛት ይችላሉ።
3.ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ የቀረበ የጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና (Un-conditional Bid) ከጠቅላላው ዋጋ 0.5% ሆኖ ከ500,000 ብር በላይ የሚበልጥ ከሆነ ብር 500,000 ብቻ CPO ወይም ባንክ ጋራንት በማሰራት ለብቻዉ በማሸግ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከባንክ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ለ180 ቀን ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል።
4.የሚቀርቡ ማሽነሪዎች በሙሉ የፈረስ ጉልበታቸው፣ የስሪት ዘመናቸው እና ሌሎች መጫረቻ ሰነዱ ላይ የተገለጹ መስፈርቶችን የሚያሟሉ መሆን አለባቸው።
5.የሚቀርቡ ማሽነሪዎች ወደ ሥራ በሚሰማሩበት ጊዜ እና ከአንዱ ፕሮጀክት ወደ ሌላ ፕሮጀክት ማሽነሮችን ማንቀሳቀስ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ አሸናፊው ድርጅት በራሳቸው ወጪ አጓጉዘው ወጪው በባለሥልጣኑ መ/ቤት የሚሸፈን ይሆናል።
6.የሚቀርቡ ማሽነሪዎች የኢንጂን ሠዓታቸው እና የነዳጅ ኦዲዮሜትር በትክክል የሚሠራ መሆን አለበት፡፡
7.ከዚህ በፊት ከሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን ጋር ውለታ ገብቶ በአፈጻጸም ችግር ምክንያት ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት ማሽነሪዎችን ወደ ሥራ ያላስገባና ውላቸው የተቋረጠ የማሽነሪ አከራይ ድርጅት የጨረታ ሰነዱን መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችልም።
8.የጨረታ ሰነዱ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ ጨረታ ማሰከበርያ /Bid Security/፣ ፋይናሻል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒ ሰነዶችን በተለያየ ፖስታ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ ተካተውና በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመጻፍ ሕጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት በሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን በግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ክፍል ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ማስከበሪያው ከቴክኒካል ሠነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት። ከላይ የተጠቀሰው ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የእረፍት ወይም የሕዝብ በዓል ቀን ሆኖ ከዋለ በቀጣይ በሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ የሚከፈት ይሆናል።
9. በጨረታ ሰነድ ላይ የተጠቀሱትን የጨረታ መመሪያ እና ሕጎች አለማክበር በመጫረቻ ሰነዶቻቸው በሁሉም ገጽ ላይ ማህተምና ፊርማ ያለማድረግ እና ያልተፈረመበት ስርዝ ድልዝ ያለበት የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
10.ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ የጨረታ መክፈቻ ተብሎ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ በባለሥልጣኑ መ/ቤት አዳራሽ ይከፈታል።
ማሳሰቢያ፡- ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር፡- 0462-128-446
ሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን
ሀዋሳ
Tender details
- Deadline: 2026-10-22
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 6፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-22 14:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
- Region: Sidama
- Publishing entity: Sidama Roads Authority
- Bid bond: ከጠቅላላው ዋጋ 0.5% ሆኖ ከ500,000 ብር በላይ የሚበልጥ ከሆነ ብር 500,000 ብቻ
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 12, 2026)
- Posted at: 2026-10-13T08:43:41.000Z
- Source: Qelal Tenders