Food Items and Drinks
የጭልጋ ወረዳ ማረሚያ ቤት አስተዳደር ጽ/ቤት ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ ቡድን መሪ በበጀት ዓመቱ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጭልጋ ወረዳ ማረሚያ ቤት አስተዳደር ጽ/ቤት ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ ቡድን መሪ በበጀት ዓመቱ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1. የእህል አቅርቦት፣
- ሎት 2. የወጥ ማጣፈጫ፣
- ሎት 3. የማገዶ እንጨት፣
- ሎት 4. አትክልት፣
- ሎት 5. የምግብ ዘይት እና ፊኖ ለአንድ ዓመት የሚቆይ ከተቋሙ ድረስ የሚያቀርቡ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።
- የዘመኑን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው።
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማሰረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) የሚያቀርቡ።
- የግዥው መጠኑ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ የማይመለስ ብር 50 (ሃምሳ ብር) በመክፈል ለግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 02 ድረስ በመምጣት መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ የሚሞሉትን አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታ አሸናፊ ድረጅት የአሸነፈውን ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታው አሸናፊ ድርጅት የአሸነፈውን እቃ ጭልጋ ማረ/ቤት መጋዘን ድረስ የሚያቀርብ መሆኑን አለበት።
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ቅጅዎች ማለትም ዋናውንና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ጭልጋ ወረዳ ማ/ቤት አስ/ጽ/ቤት ግዥ /ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በተከታታይ ቀናት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ከጥቅምት 02/2019 እስከ ጥቅምት 13/2019 ዓ.ም 11፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታው ሳጥን ጥቅምት16/2019 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ላይ ይታሸጋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ ቡድን መሪ ጥቅምት 16/2019 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡30 ይከፈታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃና ማብራሪያ ከፈለጉ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 333 22 02 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
ማሳሰቢያ፡-
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ይገኛል።
- በሎት የተዘረዘሩትን እቃዎች በጥቅል ዋጋቸው አሸናፊው ይለያል።
የጭልጋ ወረዳ ማረሚያ ቤት አስ/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-26
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-10-26 10:30
- Region: Amhara
- Publishing entity: Chilga Woreda Correctional Facility
- Bid bond: 1%
- Bid document price: 50.00 ብር
- Published on: Be'kur (Oct 12, 2026)
- Posted at: 2026-10-13T12:41:25.000Z
- Source: Qelal Tenders