Tour and Travel
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በመላ አገሪቱ በሚገኙ የሥራ ቦታዎቹ እንደየፍላጎቱ የተሽከርካሪ ኪራይ አገልግሎት የሚሰጡ አስተማማኝ አጋሮችን ይፈልጋል
Description
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ - የተሳትፎ ፍላጎት ማሳወቂያ (EOI) ጥሪ
የተሽከርካሪ ኪራይ አገልግሎት አቅራቢዎችን ለማወዳደር የወጣ
የተሳትፎ ፍላጎት ማሳወቂያ መለያ ቁጥር (EOI Reference):
ይፋ የተደረገበት ቀን፡ ማክሰኞ፣ ጥቅምት 03 ቀን 2019 ዓ.ም.
የማመልከቻው መዝጊያ ቀን፡ ሰኞ፣ ጥቅምት 16 ቀን 2019 ዓ.ም.
አዘጋጅ፡ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ
ጨረታ ማስገቢያ የኢሜይል አድራሻ: [email protected]
1. (AIMS AND OBJECTIVES)
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በመላ አገሪቱ በሚገኙ የሥራ ቦታዎቹ እንደየፍላጎቱ የተሸከርካሪ ኪራይ አገልግሎት የሚሰጡ አስተማማኝ አጋሮችን ይፈልጋል። በዚህም መሠረት ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ብቁ የሆኑ የተሸከርካሪ ኪራይ አገልግሎት አቅራቢዎችን ለመለየት ይህንን የተሳትፎ ፍላጎት ማሳወቂያ (EOI) አውጥቷል። ፍላጎትና አቅም ያላቸው አቅራቢዎች በመላ አገሪቱ ለሚገኙ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ሠራተኞች በሚፈለገው መጠን እና በሚደረገው የአገልግሎት ስምምነት (SLA) መሠረት በሁሉም የሥራ ፈረቃዎች የተሸከርካሪ ኪራይ አገልግሎት ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል። ይህ የተሳትፎ ፍላጎት ማሳወቂያ ጥሪ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሚጠብቀውን የአገልግሎት ደረጃ በሚያሟላ መልኩ አገልግሎቱን በጥራትና በተሻለ አኳኋን ለማቅረብ የሚያስችል በቂ አቅም ያላቸውን አቅራቢዎች ለመለየት ያለመ ነው
2. የተሳትፎ ፍላጎት ማሳወቂያ መስፈርቶች (EOI REQUIREMENTS)
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በዚህ ዘርፍ ፍላጎትና አቅም ያላቸው የተሸከርካሪ ኪራይ አገልግሎት አቅራቢዎች ከታች የተዘረዘሩትን መረጃዎችና ሰነዶች በማያያዝ የተሳትፎ ፍላጎታቸውን እንዲያሳውቁ ይጠይቃል፡
- አቅራቢው በሁሉም ከተሞችና የሥራ ማስኬጃ ቦታዎች በመላ አገሪቱ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የተረጋገጠ አቅም እና የሥራ ልምድ ሊኖረው ይገባል።
- አቅራቢው የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ሊኖረው ይገባል።
- የድርጅቱ መገለጫ (Company Profile)፣ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ሰነድ እና የመመሥረቻ ጽሑፍ (Memorandum of Association)።
- በተሸከርካሪ ኪራይ አገልግሎት አቅራቢነት የቆየበት የሥራ ልምድ ዓመታት፤ አነስተኛው መስፈርት ሁለት (2) ዓመት ነው።
- የድርጅቱን የፋይናንስ አቅም የሚያረጋግጥ የተረጋገጠ የኦዲት ሪፖርት እና/ወይም የባንክ ሂሳብ መግለጫ (Audited Statement of Accounts / Bank Statement)።
- የተሸከርካሪዎችን እንቅስቃሴ የመከታተልና ወቅታዊ መረጃ የመስጠት ማረጋገጫ — የተከራዩ ተሸከርካሪዎች የሚገኙበትን ቦታ የሚያሳይ መረጃ በሣምንት 7 ቀን፣ በቀን 24 ሰዓት (24/7) የማግኘት ዕድል ማመቻቸት።
- የጂፒኤስ (GPS) መከታተያ የተገጠመላቸውና ለጉዞ ብቁ የሆኑ ተሸከርካሪዎችን እንዲሁም የተከላካይ አነዳድ (Defensive Driving) ሥልጠና የወሰዱ አሽከርካሪዎችን በማቅረብ የድርጅታችንን የደኅንነት መሥፈርቶች ማሟላት የሚችል
3. በተጫራቾች የሚሞላ የአሠራር ደንብ ማክበሪያ ማረጋገጫ (STATEMENT OF COMPLIANCE)
ተወዳዳሪዎች የሚከተለውን የማረጋገጫ ቅጽ ሞልተው በፊርማና ማህተም ማረጋገጥ አለባቸው፡
| ተ.ቁ (#) | የዝርዝር መግለጫ (Item Description) | አሟላለሁ/አላሟላም (Comply Yes/No) | አስተያየት (Remarks) |
| ሀ | ከመጀመሪያው ግንኙነት ጀምሮ በስምምነቱ (SLA) መሠረት በኢትዮጵያ ውስጥ በየትኛውም ቦታ ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት 24/7 ያለማቋረጥ ለማቅረብ ቁርጠኝነት። | ||
| ለ | በተስማማነው ውልና ሁኔታዎች መሠረት የታሰበውን የተሸከርካሪ ኪራይ አገልግሎት ለመስጠት ከሚመለከተው አካል የተሰጠ ፈቃድ ያለው | ||
| ሐ | ከተሸከርካሪ እና ትራንስፖርት አስተዳደር (Fleet & Transport Management) ቡድን ጋር በመመካከር የተሸከርካሪ ኪራይ አገልግሎቱን በብቃት ማመቻቸት። | ||
| መ | ለጉዞ ብቁ የሆኑ ተሸከርካሪዎችን፣ የሠለጠኑ አሽከርካሪዎችን እና አገልግሎቶችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለማቅረብ የሚያስችል የተረጋገጠ አቅም። | ||
| ሠ | የሳፋሪኮምን ፍጹም የደኅንነት ደንቦች (Safaricom Absolute Safety Rules) ማክበር። | ||
| ረ | የተከራዩትን ሁሉንም ተሸከርካሪዎች መከታተል እና በሚፈለግበት ጊዜ ሁሉ መረጃውን ማቅረብ የሚችል። | ||
| ሰ | ድርጅቱ ለሥራው የሚያስፈልጉትን ማናቸውንም ዓይነት ተሸከርካሪዎች (ሴዳን፣ ኤስ.ዩ.ቪ፣ ፒክ አፕ፣ ቫን እና/ወይም ሌሎች) ለአጭርም ሆነ ለረጅም ጊዜ አገልግሎት በተስማማነው የማስረከቢያ ጊዜ ውስጥ ማቅረብ የሚችል። |
- የተፈቀደለት ተወካይ ስም (Name of Authorized Representative): ___________________________
- ፊርማ (Signature): ___________________________
- ቀን (Date): ___________________________
- የድርጅቱ ማህተም (Company Stamp): ___________________________
4. ማመልከቻ የማስገቢያ ሁኔታ (SUBMISSION OF RESPONSES)
ፍላጎት ያላቸው አቅራቢዎች ከላይ የተዘረዘሩትን ሰነዶች እና የተፈረመውን የአሠራር ደንብ ማክበሪያ ማረጋገጫ ሰነድ በማካተት ማመልከቻቸውን በሚከተለው የኢሜይል አድራሻ መላክ አለባቸው 5. የኢሜይል አድራሻ፡ [email protected] 6. የማመልከቻው መዝጊያ ቀን፡ እስከ ሰኞ፣ ጥቅምት 16 ቀን 2019 ዓ.ም. ድረስ የማመልከቻ ማስታወሻዎች፡
- በኢሜይል የሚላኩ ማናቸውም ሰነዶች መጠን ከ20 ሜጋ ባይት (20MB) መብለጥ የለበትም።
- መጠኑ ከዚህ በላይ ከሆነ በGoogle Drive ማስፈንጠሪያ (link) ያጋሩ።
- እባክዎ የኢሜይሉን ርዕስ፡ “PROVISION OF VEHICLE RENTAL SERVICES” በማለት ይጥቀሱ።
- በዚህ የተሳትፎ ፍላጎት ማሳወቂያ (EOI) ደረጃ ምንም ዓይነት የዋጋ ዝርዝር መላክ የለበትም።
- ማስታወቂያው የሚወጣበት ቀን ይህ መረጃ በሁሉም የመገናኛ ብዙኃን የሚለቀቅበት ቀን ይሆናል።
- የማብቂያው ቀን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ14 የካላንደር ቀናት በኋላ ይሆናል።
5. ቀጣይ እርምጃዎች (NEXT STEPS)
ማመልከቻዎቹ ከተቀበሉ በኋላ ቀጣዩ ሂደት የሚከተሉትን ደረጃዎች ይከተላል፡
- የቀረቡትን የተሳትፎ ፍላጎት ማሳወቂያዎች መገምገም እና ብቁ የሆኑትን አቅራቢዎች መለየት (Shortlisting)።
- የአቅራቢዎችን ብቃት ማረጋገጥ እና ወደ ሥርዓት ማስገባት (Supplier onboarding and qualification)።
- ብቁ ለተባሉ አቅራቢዎች ሙሉ የጨረታ ሰነድ ማውጣት (Issuing tender to prequalified suppliers)።
6. ጠቃሚ ማስታወሻዎች (IMPORTANT NOTES)
- ለቀጣይ ውይይት የሚመረጡት ዝቅተኛውን መስፈርት የሚያሟሉ አቅራቢዎች ብቻ ናቸው።
- በዚህ የተሳትፎ ፍላጎት ማሳወቂያ (EOI) ደረጃ ምንም ዓይነት የዋጋ ዝርዝር መላክ የለበትም።
- ይህ የተሳትፎ ፍላጎት ማሳወቂያ ሰነድ መድረሱ ብቻ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያን ወደ ምንም ዓይነት የውል ስምምነት አያስገባውም። ማንኛውም ዓይነት የውል ስምምነት የሚፈጸመው የጨረታ ሂደቱ ተጠናቆ አሸናፊ ለሆነው ተጫራች የሥራ ሽልማት ደብዳቤ (Award) ሲሰጥ ብቻ ነው።
- ለዚህ ማመልከቻ ዝግጅትና ማቅረቢያ የሚወጣውን ማናቸውንም ወጪ ተወዳዳሪው ራሱ ይሸፍናል።
- ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ለዚህ ጥሪ የቀረቡለትን ማናቸውንም ወይም ሁሉንም ፕሮፖዛሎች ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመቀበል ወይም ውድቅ የማድረግ ሙሉ መብቱ የተጠበቀ ነው። የሚሰጠው ማንኛውም ውሳኔ የመጨረሻ ሲሆን፣ ለተወዳዳሪዎች የሂደቱን ውጤት ከማሳወቅ ውጭ ምንም ዓይነት ልውውጥ አይደረግም።
- ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እና ሕጋዊ ተወካዮቹ ከዚህ ማመልከቻ ጋር ተያይዘው የቀረቡትን ሰነዶችና መረጃዎች ትክክለኛነት ለማጣራት ማናቸውንም ምርመራ ወይም ማጣራት የማካሄድ ሙሉ ፈቃድ ተሰጥቷቸዋል።
Tender details
- Deadline: 2026-10-26
- Bid closing time: 17:00
- Bid opening: 2026-10-26 17:00
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀን እና ሰዓት አልተገለጸም
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Safaricom Ethiopia
- Buyer TIN: 0073915295
- Published on: Reporter (Oct 14, 2026)
- Posted at: 2026-10-14T07:46:54.000Z
- Source: Qelal Tenders