Insurance Service

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ በስሩ ለሚገኙ ተቋማት አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ በስሩ ለሚገኙ ተቋማት አገልግሎት የሚውል፡-

  • ሎት 1 አመታዊ የመኪና መድን ዋስትና /ኢንሹራንስ
  • ሎት 2 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
  • ሎት 3 ለባህል ቱሪዝም መምሪያ አገልግሎት የሚውል የቦክስ ሪንግ ማቴሪያል ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ ተጫራቾች መሠዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለፅን፡- ማቅረብ የምትችሉት መረጃ፡-

  1. የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ
  2. የግብርመለያ ቁጥር TIN/ያላቸው
  3. የዘመኑን ታክስ ለመክፈላቸው ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል
  4. የገንዘብ መጠኑ ከ500,000 ሺህ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን ይኖርበታል
  5. ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. የሚገዛዉን ግዥ ዝርዝርመግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ/ቢድ ቦንድ/ ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ላይ 1% በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ/ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200/መቶ/በመክፈል ጎን/ከ/አስ/ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 15 መውሰድ ይችላሉ፡፡
  9. ተጫራቾች የመጫረቻ ሃሳባቸውን አንድ ወጥ በሆኑ ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በመሙላት በታሸገ ፖስታ ጎን/ከ/አስ/ግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ስዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ተጫራቶች ዋጋውን በሚሞሉበት ወቅት ስርዝ ድልዝ ካለ ከውድድር ውጭ ያስደርጋል
  11. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ሙሉ ስምና ፊርማቸውን የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው
  12. ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት በጎንደር ከ/አስ/ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 11 በመምጣት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጥዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሆኖ ጥሪአችንን አክብረዉ ባይገኙም ጨረታዉ በሌሉበት ይከፈታል፡፡ የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን በተጠቀሰዉ ሰአት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  13. ማንኛውም ተጫራች የሚቀርብ ቅሬታ ካለ ጨረታው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 5 የስራ ቀን ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ከ5 የስራ ቀናት በኋላ የሚቀርብ ቅሬታ መ/ቤታችን የማንቀበል መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  14. የቦክስ ሪንግ እና ኤሌክተሮኒክስ እቃወች በራሱ ትራንስፖርት ጎ/ከ/አስ/ገንዘብ መምሪያ ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ለአመታዊ ኢንሹራንስ ጎ/ከ/አስተዳደር ህጋዊ ቢሮ/ተቋም ያለው መሆን አለበት
  15. ጨረታ ሲከፈት የተነበበው ወጋ እና የሂሳብ ስሌት ሲሰራ በሚገኘው ዋጋ ላይ እስከ 3% ልዩነት ከተገኝ ተቀባይነት ሲኖረው ወደ ታችም ሆነ ወደ ላይ ከ3% በላይ ልዩነት ካለ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡ዋጋን ደምሮ አለማስቀመጥም ከውድድር ውጭ ያስደርጋል፡፡
  16. ለተጨማሪ መረጃ ካስፈለገ ጎን/ከተ/አስ/ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 5 በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 058 126 03 06 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  17. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

P.O.Box 192 Tele: 0581-26-03-06
Fax: 0581 11 7563 email: [email protected] 
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ


Tender details

  • Deadline: 2026-10-24
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጥዋቱ 4፡00
  • Bid opening: 2026-10-24 10:30
  • Bid opening (note): ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጥዋቱ 4፡30
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Gonder City Administration FEDB
  • Bid bond: 1%
  • Bid document price: ብር 200/መቶ/
  • Published on: Addis Zemen (Oct 14, 2026)
  • Posted at: 2026-10-14T08:43:10.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders