Land Lease & Real Estate

በአብክመ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በዳዋ ጨፋ ወረዳ አስተዳደር የሸክላ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት ለንግድ እና ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውሉ የልማት ቦታን በመደበኛ ጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ማስተላለፍ ይፈልጋል

Description

የስድስተኛ ዙር የመሬት ሽያጭ የሊዝ
ጨረታ ማስታወቂያ

በአብክመ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በዳዋ ጨፋ ወረዳ አስተዳደር የሸክላ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 ከ ሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት በሸክላ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ጠቅላላ ስፋቱ 3003(ሶስት ሺ ሶስት) ካሬ ሜትር የሆነ ለንግድ እና ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውሉ የልማት ቦታን በመደበኛ ጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታው ላይ ለመሳተፍ ፍቃድኛ የሆኑ ተጫራቾች :-

  1. የጨረታውን ሰነድ በሸክላ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት በመሬት ልማትና ባንክ ቡድን ቢሮ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ሸያጭ የማይመለስ የኢትዮ. ብር 400.00 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች ቦታወቹ የሚገኙበት ድረስ በመሄድ አጠቃላይ የቦታውን ሁኔታ በማየት ዋጋ ማቅረብ ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ ሰነድ ላይ በቀረበው ስፔስፊኬሽን / Specifection/ መሰረት መሆን ይኖርበታል፡፡
  4. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ጠቅላላ ቦታ ስፋት በሊዝ መነሻ ዋጋ ተባዝቶ ከሚገኘው ውጤት 50 በመቶ ያላነሰ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ ክፍያ ማዘዣ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር ወይንም ከ 50 ከመቶ ቢያንስ ተጫራቹ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከውድድር ይሰረዛል።
  5. ተጫራች የጨረታውን ሰነድ፣ ሲፒኦ እና ሌሎች የጨረታ ሰነዶችን በታሸገ ኤንቨሎፕ በአብክመ በኦ/ብ/ ዞን በሸክላ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት በመሬት ልማትና ባንክ ቡድን ቢሮ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን 04/02/2019 ዓ.ም እስከ 17/02/2019 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ጨረታው የሚዘጋበት ቀን በ17/02/2019 ዓ.ም 11፡00 ሰዓትይሆናል፡፡
  7. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በ 18/02/2019 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት በሸክላ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት አዳራሽ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  8. ቦታውን ለመጎብኘት ለሚፈልጉ ተጫራቾች ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት ለሽያጭ የተዘጋጁ ቦታዎች በሚገኙበት የሸክላ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት በሚመድባቸው አስጎብኝዎች ቦታዎቹን መመልከትይችላሉ፡፡
  9. የአካበቢውን ወቅታዊ የሊዝ ጨረታ መነሻ ዋጋ እና ሌሎች የከተማ መሬትን በሊዝ ለማስተዳደር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 721/2004 መሰረት በማድረግ የሸክላ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ መመልከትይችላሉ፡፡
  10. የሸክላ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨረማሪ መረጃ ፡-በስልክ ቁጥሮች
0920960730/0923661118 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ
በአብክመ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በዳዋ ጨፋ ወረዳ የሸክላ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-27
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid opening: 2026-10-28 10:00
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Dawa Chefa Woreda Shekla City Hall
  • Bid bond: በሚወዳደሩበት ጠቅላላ ቦታ ስፋት በሊዝ መነሻ ዋጋ ተባዝቶ ከሚገኘው ውጤት 50 በመቶ ያላነሰ
  • Bid document price: 400.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published on: Addis Zemen (Oct 14, 2026)
  • Posted at: 2026-10-14T08:55:45.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders