Hand Tools and Workshop Equipment

ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ.የተ.የግ.ማህበር የወርክሾፕ ዕቃዎች እና የእጅ መሳሪያዎች ግዥን በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር EC 001/2019

1. ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ.የተ.የግ.ማህበር የወርክሾፕ ዕቃዎች እና የእጅ መሳሪያዎች ግዥን በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከጥቅምት 4 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 11 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 - 6፡30 እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከ7፡30 -11፡00 ድረስ “ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ.የተ.የግ.ማ ጉርድ ሾላ ሴንቸሪ ሞል ፊት ለፊት ወይም ላሜ ዴያሪ ጀርባ ከኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ አጠገብ በሚገኘው የኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ.የተ.የግ.ማ ሕንጻ ላይ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 106 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200.00 ብር /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል እና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር መለያ ቁጥር ያላቸው፤ የታክስ ክሊራንስ ሰርተፍኬት፣ የአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ እና የሻት ምዝገባ ሰርተፍኬት ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በመያዝ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት

  • አንድ ዋና /Original/ የጨረታ ሰነድ ለብቻው በሰም በታሸገ ፖስታ ታሽጐ
  • አንድ ቅጂ /Copy/ የጨረታ ሰነድ ለየብቻው በታሸገ ፖስታ ታሽጐ እንዲሁም፣
  • ሁሉም በአንድ ላይ በትልቅ ፖስታ ውስጥ ተካቶ የታሸገ መሆን አለበት።
  • በዋናውና በቅጂው መካከል ልዩነት ቢፈጠር ዋናው ተቀባይነት ይኖረዋል። ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም። የተሰረዘ ሰነድ በፊርማ መረጋገጥ ይኖርበታል።

4. ተጫራቾች የወርክሾፕ ዕቃዎች እና የእጅ መሳሪያዎች ግዥ የሚያቀርቡበትን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋ 2% /ሁለት ከመቶ/ የባንክ ክፍያ ማዘዣ /CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ (unconditional) ባንክ ጋራንቲ ለኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ.የተ.የግ.ማ በሚል ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ቀን ጥቅምት 11 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 208 ሲሆን፣ ጨረታውን የመክፈቻ ቀን ጥቅምት 11 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተዘግቶ 4:45 ላይ ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 106 ይሆናል።

6. ከላይ የተገለጸውን መመሪያ ባልተከተሉ ተጫራቾች ላይ ወዲያውኑ ከጨረታው የሚሠረዝ መሆኑን እንገልጻለን።

7. ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 09-11-93-73-75 መጠቀም ይችላሉ።

8. ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ.የተ.የግ.ማ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ.የተ.የግ.ማህበር


Tender details

  • Deadline: 2026-10-21
  • Bid closing time: 10:30
  • Bid opening: 2026-10-21 10:45
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethio Agri-CEFT Pvt.Ltd.Co.
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 14, 2026)
  • Posted at: 2026-10-14T10:03:44.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders