Building Construction

የአምቦ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽሕፈት ቤት በ2019 በጀት ዓመት የሚከናወኑ የገበያ ማዕከል፣ ሚኒ-ብሪጅ (Mini-Bridge)፣ የባህል ፍርድ ቤት ህንፃ (Traditional Court hall) እና የመንገድ ላይ መብራት (Street Light) ግንባታ ሥራዎችን ሕጋዊ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ኮንትራክተሮችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል

Description

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 02/2019

የአምቦ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ፅ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት የሚዉሉ “MiniBridge”፤ G+2 የገበያ ማዕከል ህንፃ፤ “Traditional Court hall” ህንፃ ግንባታ እና የመንገድ ላይ መብራትን ለማስገንባት አስፈላጊ የሆኑ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ኮንትራክተሮችን በማወዳደር ለማሰራት ለሚፈልግ፤

ተ/ቁ

የስራ ዓይነት

ደረጃ

ኮንትራክተር

1

G+2 የገቢያ ማዕከል ህንፃ

4 እና ከዚያ በላይ

GC,BC

2

"Mini-Bridge"

4 እና ከዚያ በላይ

GC,RC

3

Traditional Court hall/ Mana murtii Aadaa OL-daharfataa"

4 እና ከዚያ በላይ

GC,BC

4

የመንገድ ላይ መብራት Street Light/

4 እና ከዚያ በላይ

Electro Mechanical

 

  1. ከተጠቀሰው ስራ ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያለው የ 2019 ዓ/ም የታደሰ ንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የከፈለ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin Number/ ያለው፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ/VAT/ ተመዝጋቢ፤ እንዲሁም በአቅራቢዎች ዝርዝር/Supplier List/ የተመዘገበ ሆኖ ከሚመለከተው አካል የማስረጃውን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል ፤ በተጨማሪም ከሚያገኘው ገቢ ላይ 3% ታክስ ለመክፈል ፈቃደኛ የሆነ፤
  2. ከሙስና እና መሰል ብልሹ አሰራር ድርጊቶች ነፃ የሆነ የክልሉንና የአገሪቱን ሕግ የሚያከብር፤
  3. በአምቦ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ፅ/ቤት ስም ብር 500,000 CPO የጨረታ ማሰከበሪያ ማስያዝ የሚችል፤
  4. በጨረታ ሰነዱ ላይ ስልጣን ባለዉ አካል /የድርጅቱ ባለቤት/ ስም፤ ፊርማ፤ የድርጅቱ  ማህተም ፤ የድርጅቱ ሙሉ አድራሻ እና ስልክ ቁጥር በፖስታ ላይ መግለፅ የሚችል፤
  5. ተጫራቾች የጨረታውን ቴክኒካል፤ ፋይናንሻል እና CPO ኦሪጂናል እና የቴክኒካል፤ ፋይናንሻል እና CPO ኮፒዎቻቸው በታሸገ ፖስታ አድርጎ ማቅረብ አለበት።
  6. ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 20 ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ21 ቀን በ24/02/2019ዓ/ም በ8፡15 የጨረታው ሳጥን ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ8፡45ሰዓት ይከፈታል።
  7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በአምቦ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ክፍል ይከፈታል። ጨረታው በሚከፈትበት ቀን ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባለመገኘታቸው ምክንያት ጨረታውን ከመከፈት አየስቀርም፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት የአድራሻ ለውጥ ካለ በውስጥ ማስታወቂያ የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን።
  8.  እያንዳነዱን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 2000/ሁለት ሺህ ብር/ በመክፈል በአምቦ ከተማ ገንዘብ ፅ/ቤት ስም በTele birr short Code 518219 እና Operator ld 182149 በማስገባት ደረሰኙን በአምቦ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ፅ/ቤት ገቢ በማድረግ ሰነዱን በአምቦ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ፅ/ቤት መዉሰድ ይቻላል።
  9.  አሸናፊ የሆነ ተጫራች አሸናፊ የሆነበትን ስራ በደብዳቤ ከተሰጠው ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከ/ቤቱ ጋር ውል መፈረም አለበት።
  10. ጨረታዉን ለማደናቀፍ የሚሞክር ተጫራች ከጨረታዉ ዉጪ እንዲሆን ተደርጎ ለወደፊቱ በማንኛውም የመንግስት ግዥ እንዳይሳተፍ ይደረጋል።
  11.  መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ከገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፦ በኦሮሚያ ክልል ምዕ/ሸዋ ዞን የአምቦ  ከተማ አስተዳደር ገንዘብ  ጽ/ቤት

የአምቦ ከተማ  አስተዳደር ገንዘብ  ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-03
  • Bid closing time: 14:15
  • Bid opening: 2026-11-03 14:45
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Ambo City Finance and Economic Development Bureau
  • Bid bond: 500,000.00 ብር
  • Bid document price: 2000.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published on: Addis Zemen (Oct 14, 2026)
  • Posted at: 2026-10-14T10:59:02.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders