Audio Visual, Photography and Filming Service and Equipment

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን (ECMA) ባለው በጀት የኦዲዮ ቪዥዋል ፕሮዳክሽን አገልግሎት (Audio-Visual Production Services) በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፦ EGMA/NCB/OB/04/2019

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን  ባለው በጀት የኦዶ ቪዥዋል ፕሮዳክሽን አገልግሎት ግዥ (Procurement of Audio-visional Production services) በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎቱን ለመግዛት ይፈልጋል::

በዚሁ መሰረት፦

  1. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታው ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መክፈቻ ቀን ድረስ የማይመለስ 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመ/ቤታችን አካውንት 1000586364824 ገቢ በማድረግ ከባለስልጣኑ ፋይናንስና ግዥ ክፍል የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ::
  2. ተጫራቾች የመወዳደርያ ሰነዳቸውን ፋይናንስና ቴክኒካል ኦሪጅናልና ኮፒ ለየብቻ በማሸግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ጨረታው መዝጊያ ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
  3. ተጫራቾች በዘርፉ ያላቸውን በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ!የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣የግብር ክሊራንስ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤ በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረገጽ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማስረጃቸውን እንዲሁም የተፈረመና ማህተም ያለው የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈፀም ቃል የተገባበት ቅጽ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል::
  4.  ተጫራቾች ዋጋቸውን በመሙላት ባለስልጣኑ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከጨረታ መዝጊያ ሰአት በፊት ማስገባት አለባቸው:: ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርቡና ስርዝ ድልዝ ያለው የጨረታ መወዳደሪያ ሰነድ ተቀባይነት የለውም::
  5. ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ለ15 ቀናት ብቻ ነው::
  6. ተጫራቾች በሚያቀርቧቸው ሰነዶች ላይ የድርጅታቸውን ማህተምና የተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪል ፊርማ መኖር ይገባዋል::
  7. አሸናፊው ተጫራች አገልግሎቱ በተፈለገ ጊዜ አገልግሎቱን የመስጠት ሃላፊነት አለበት::
  8. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበርያነት የብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ዋስትና ወይም ሲፒኦ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል::
  9. ተጫራቾች የቀረበውን ዝርዝር መስፈርት መሰረት በማድረግ የሚያቀርቡትን አገልግሎት ዝርዝር የቴክኒክ መግለጫ - ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል::
  10. አንዱ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም::
  11. ጨረታው ጥቅምት 18 ቀን 2019 ከሰዓት 8:30 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከሰዓት በ 11:00 ላይ ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በባለስልጣኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል::
  12. በጨረታው መክፈቻ ዕለት የተጫራቾች አለመኖር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉለውም::
  13. ባለስልጣኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  14. ተጨማሪ ማብራርያ ካስፈለገ በአካል የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን አድራሻ ቦሌ መንገድ ፍላሚንጎ ሪስቶራንት ገባ ብሎ ባለው ዋ/መ/ቤት በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ::

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን

የፋይናንስና ግዥ ዳይሬክቶሬት

ከፍላሚንጎ ሪስቶራንት ወደ አደራ ሆስፒታል በሚወስደው

መንገድ ምናዬ ህንፃ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

ስልክ 011-5-57-83-27

ኢሜል: [email protected]


Tender details

  • Deadline: 2026-10-28
  • Bid closing time: 14:30
  • Bid opening: 2026-10-28 17:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Reporter (Oct 14, 2026)
  • Posted at: 2026-10-14T12:03:32.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders