Building Construction
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር በልደታ የሚገኘውን የፍራንቻይዝ የሽያጭ ማዕከል በኢትዮ ቴሌኮም ስታንዳርድ መሠረት እድሳት ለማስደረግ (ሎት 1) እና የውኃ ፓምፕ ለመግዛት (ሎት 2) ሕጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት እና መግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
CNNCB/9/19
የድርጅታችን ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል/ማህበር
- ሎት 1 ልደታ የሚገኘውን የፍራንቻይዝ የሽያጭ ማዕከል በኢትዮ ቴሌኮም ስታንዳርድ መሰረት እድሳት ለማስደረግ ተፈልጓል:: በመሆኑም የዕድሳት ስራውን ማከናወን የሚችሉ ደረጃ 5 እና በላይ ያላችሁ
- ሎት 2- የውኃ ፓምፕ ማቅረብ የምትችሉ ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣
በጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ መሆኑን የሚገልጽ ደብዳቤ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡትን ማስረጃ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ እና የዕቃው ወይም የአገልግሎቱ ዝርዝር መግለጫ በተለየ በሰም በታሸገ ፖስታ እንዲሁም ዕቃዎቹን የምታቀርቡባቸውን ዋጋ በተለየ በሰም በታሸገ ሁለተኛ ፖስታ በማድረግ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል:: የጨረታ ዶክመንቱን ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ የግዢ ዋና ክፍል ብር 100.00 በመክፈል ከሰኞ እስከ ዓርብ (ጠዋት 2፡00-6፡00 እንዲሁም ከሠዓት 7፡00-10፡30) እና ቅዳሜ ግማሽ ቀን (ጠዋት 2፡00-6፡00) ማግኘት ይቻላል:: የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1 ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ) እንዲሁም ለሎት 2 ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ. ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከመጫረቻ ዶክመንት ጋር መቅረብ ይኖርበታል::
ተጫራቾች የመጫረቻ ዶክመንታቸውን ከላይ በተጠቀሰው አድራሻና የሥራ ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ጥቅምት 19 ቀን 2019 ዓ.ም 4፡00 ጠዋት ድረስ ማስገባት ይችላሉ:: ጨረታው በዚሁ ዕለት በ 4፡30 ጠዋት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል:: ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ያላሟላ ተጫራች ያለተጨማሪ ማስታወቂያ ከውድድሩ ዉጪ ይደረጋል::
ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሱ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ
ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት
ህንፃ 5ኛ ፎቅ
ስልክ ቁጥር 011-1-569992
አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
Tender details
- Deadline: 2026-10-29
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-10-29 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Commercial Nominees P.L.C.
- Buyer TIN: 0000958158
- Buyer address: ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published on: Reporter (Oct 14, 2026)
- Posted at: 2026-10-14T12:30:06.000Z
- Buyer website: https://commercialnominees.com/
- Source: Qelal Tenders