Construction Machinery and Equipment
የፉሪ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽሕፈት ቤት ለፉሪ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ጽሕፈት ቤት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የግንባታ ማሽነሪዎች፣ የሰው እና ደረቅ ጭነት እንዲሁም ደብል ጋቢና ፒካፕ ተሽከርካሪዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የፉሪ ክ/ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለፉሪ ክ/ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የግንባታ ማሽነሪዎች፤ የሰው እና ደረቅ ጭነት ፤ ደብል ጋቢና ፒካፕ መኪናዎችና ተሽከርካሪዎችን ለተለያዩ አገልግሎቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ስለሚፈልግ ህጋዊ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው የተጫራቾች መመሪያ መሠረት ጨረታውን እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል፡፡
ዝርዝር ሁኔታዎች
የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከፉሪ ክ/ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 1000.00 (አንድ ሺህ ብር) በሲንቄ ባንክ ሂሳቢ ቁጥር በ furi Sub city Finance office “A 1064669901216 “ የማይመለስ ብር ገቢ ስሊፑን/ Deposit slip/ ከፉሪ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት ገቢ ደረሰኝ በማስቆረጥ የጨረታ ሰነዱን ከፉሪ ክ/ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ፤ ንብረት አስተዳደር አወጋገድ እና ጠቅላላ አገልግሎት የሥራ ሂደት ክፍል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የተጫራቾች ግዴታዎች
- በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ በስማቸው ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለዚሁም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው እና ማስረጃውን ማቅረብ የሚችሉ ፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢና የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረ CPO (ሲፒኦ) ብቻ 150,000.00 (አንድ መቶ ሀምሳ ሺህ )ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
- ለማሽነሪ ኪራይ ላይ የሚሳተፉ ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ነዳጅን፤ ቅባት፤ ጥገናን እና ሌሎች ተዛማች ወጪዎችን በተጫራቹ ድርጅት (አከራይ) የሚሸፈን ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ በኋላ ማሽነሪዎችን በራሳችሁ ወጪ መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው ቦታ (ሥራ የሚሠራበት ቦታ) ድረስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባችዋል፡፡
- የሀገር ውስጥ ተወዳዳሪዎች በአቅራቢዎች ዝርዝር (EJP) የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ላይ የሚያቀርቡት ማሽነሪ ደረጃውን የጠበቀ ሆኖ የባለቤትነት ማስረጃ ወይም ሊብሬ ወይም ሕጋዊ የኪራይ ውል አያይዞ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተወዳዳሪው አሸናፊ ከሆኑ የውል ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ CPO (200,000.00 )ሁለት መቶ ሺህ )ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ በመሙላት በኦርጅናል እና በኮፒ በመለየት በፖስታ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን የመንግስት ሥራ ሰዓት ፉሪ ክ/ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ንብረት አወጋገድ እና አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት የሥራ ሂደት ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ተዘግቶ በዕለቱ 4፡30 ተጨራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ፉሪ ክ/ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥሮች:- 0910 489 372/ 0938 173 674 በመደወል መረዳት ይችላሉ፡፡
ፉሪ ክ/ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ / ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-11-02
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ጠዋት 4፡00
- Bid opening: 2026-11-02 10:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ጠዋት 4፡30
- Region: Oromia
- Publishing entity: Sheger City Administration, Furi Sub-City Finance Office
- Bid bond: 150,000.00 (አንድ መቶ ሀምሳ ሺህ ብር)
- Bid document price: 1000.00 (አንድ ሺህ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Oct 15, 2026)
- Posted at: 2026-10-15T07:31:49.000Z
- Source: Qelal Tenders