Building Construction

በደ/ም/ኢትዮ/ህ/ክ/መ/ክህሎትና ቴክኖሎጅ ቢሮ የአማን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የመማሪያ ክፍል ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል

Description

ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

በደ/ም/ኢትዮ/ህ/ክ/መ/ክህሎትና ቴክኖሎጅ ቢሮ የአማን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ባለቤትነት በ2019 የበጀት ዘመን ሊያሰራ ላሰበው የመማሪያ ክፍል ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾችን ማሰራት ይፈልጋል።

  1. በኮንስትራክሽን ዘርፍ ደረጃ 5/GC/BC እና ከዛ በላይ ፍቃድ ያላቸው።
  2. ተጫራቾች ሰነድ ለመግዛት በሚመጡበት ጊዜ ለበጀት ዓመቱ የሚያገለግል የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ፤ የታያለ የንግድ ፍቃድ ምዝገባ ወረቀት ፣ የቫት ተመዝጋቢ ሰርተፊኬት፤ የግብር ከፋይ መለያ እና ምስክር ወረቀት ዋናውንበማቅረብ በበደ/ም/ኢትዮ/ህ/ከ/መ ከህሎትና ቴክኖሎጅ ቢሮ የአማንፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅት የጨረታ ኮሚቴ የቢሮ ቁጥር 02 የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ 1000 ብር በመክፈል መግዛት ይኖርችኋል።
  3.  የአቅራቢነት ምስከር ወረቀት እና ከግብር ነፃ መሆኑን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
  4. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000 (ሀምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ ጋራንቲ (ለ120 ቀናት የሚ ቆይ) ማቅረብ የሚችል።
  5. ተጫራቾች የገዙትን ሰነድ (ፋይናንሻል እና ቴክኒካል) ከላይ የተዘረዘሩትን አስፈላጊ የሆኑትን መረጃዎች ለእያንዳንዳቸው አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ በሰም በታሸገ ፖስታ በማቅረብ የፋይናንሻል እና የቴክኒካል ዶክመንቱን በጥቅሉ በአንድ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  6. እያንዳንዱ ፖስታ በተገቢው ሁኔታ በሰም ታሽጎ ማህተም መመታት እና መፈረም አለበት።
  7. ተጫራቾች በሁሉም የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዶች ላይ የተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው ፊርማ እና እንዲሁም የድርጅቱ ማህተም መኖር አለበት።
  8. እያንዳንዱ ፖስታ የሚወዳደሩበትን የስራ ቦታ፣ የተቋራጩ አድራሻ እና ስልክ የተወካዩን ስልክ ቁጥር በመግለጽ መጻፍ አለበት።
  9. ይህ ጨረታ በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 21 ቀናት ውስጥ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ ቴክኒካል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ የፋይናንሻል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል ሁለት ኮፒ በማድረግ ማስገባት አለባቸው።
  10.  ጨረታው የሚታሸገው ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ተኛው ቀን በደ/ም/ኢትዮ/ህ/ክ/መ ክህሎትና ቴክኖሎጅ ቢሮ የአማን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅት ቢሮ ቁጥር 02 ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮቻቸው በተገኙበት ይታሸጋል።
  11. ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ተኛው ቀን በበደ/ም/ኢትዮ/ ህ/ክ/ መ ክህሎትና ቴክኖሎጅ ቢሮ የአማን ፖሊ ቶክኒክ ኮሌጅት የጨረታ ኮሚቴ የቢሮ ቁጥር 02 ከሰዓት በኋላ 7፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  12. የሳይት ምልከታው ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይ ቀናት ብቻ ይሆናል።
  13.  መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፡-0932144862/0909836114/0940946144

የደ/ም/ኢትዮ/ህ/ክ/መ ክህሎትና ቴክኖሎጅ ቢሮ

የአማን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ


Tender details

  • Deadline: 2026-11-06
  • Bid closing time: 10:30
  • Bid closing (note): ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ተኛው ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-11-06 13:30
  • Bid opening (note): ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ተኛው 7፡30 ሰዓት
  • Region: South West Ethiopia Region
  • Publishing entity: Aman Poly TVET
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 1000.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 16, 2026)
  • Posted at: 2026-10-16T07:54:53.000Z
← Back to all tenders