Machinery and Equipment

ጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ የተለያዩ የመስኖ ዕቃዎችን (ሎት 1) እና ሶፍትዌር፣ የሶፍትዌር ባለሙያ እና ስልጠና ግዢን (ሎት 2) በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ለመግዛት ያወጣው ማስታወቂያ (ማስታወቂያ ቁጥር: ጣበስፋ /አግ/ብግጨ/04/2019)

Description

ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ማስታወቂያ ቁጥር: ጣበስፋ /አግ/ብግጨ/04/2019

ጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ

  • በሎት 1 የተለያዩ የመስኖ ዕቃዎች
  • በሎት 2 ሶፍት ዌር፣ የሶፍት ዌር ባለሙያ እና ስልጠና ማለትም ስኳርን ከሞላሰስ (AH and AL) የሚለይ ኘሮግራም እና ኘሮግራሙን የሚጭን እና ስልጠና የሚሰጥ ባለሙያ የአገልግሎት ግዢ በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

1 በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች ህጋዊ የ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የታክስ ክሊራንስና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የድጋፍ ደብዳቤ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፤ ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፤ በተጨማሪም ተጫራቾች የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ወይም ሌላ አግባብነት ያለው አካል ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።

2. ጨረታው ጥቅምት 19 ቀን 2019 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ይዘጋል። ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከታች በተራ ቁጥር 4 በተገለፀው አድራሻ ጥቅምት 19 ቀን 2019 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል። ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል።

3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂ.ቁጥር 1000057735167 በመክፈልና የባንክ አድቫይስ በማቅረብ በተራ ቁ. 4 ከተመለከተው ቢሮ መግዛት ይችላሉ።

4. የጨረታው ማስረከቢያና መክፈቻ አድራሻ ቀጥሎ የተመለከተው ነው።

አዲስ አበባ ቶታል 3 ቁጥር ማዞሪያ ተዘንአ ሆስፒታል አካባቢ

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ህንጻ።

ብሎክ A ቢሮ ቁጥር B008

ስልክ ቁጥር 011 5-586725

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በየሎቱ የጠቅላላ ዋጋውን 1.5% ብር በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ ሲፒኦ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ባልተመሠረተ የባንክ ዋስትና (ጋራንቲ) ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

6. ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀናት ነው።

7. የጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ90 ቀናት ነው። ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መጃ በስልክ ቁጥር፡ 011558-67-25 ደውሎ መጠየቅ ይችላል።  

ጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ


Tender details

  • Deadline: 2026-10-29
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-10-29 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Tana Beles Sugar Factory
  • Buyer address: ካሳንቺስ ከመናኸሪያ ሆቴል  ወደ አቧሬ አቅጣጫ በሚወስደው አስፓስት መንገድ ከጨርጨር ስጋ ቤት ዝቅ በማለት የቀድሞው ተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ጊቢ ውስጥ
  • Bid bond: 1.5% በየሎቱ
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Oct 16, 2026)
  • Posted at: 2026-10-16T08:24:14.000Z
← Back to all tenders