Construction Machinery

የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የገልባጭ መኪና እስከነ ሎደሩ ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ደኢመባ 02/2019

መ/ቤታችን የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን በሥሩ ላሉት ዲስትሪክቶች አገልግሎት የሚውሉ የኮንስትራክሽን እና ኢንጅነሪንግ መሣሪያዎች መገልገያ ማለትም የገልባጭ መኪና እስከነ ሎደሩ ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።

በመሆኑም

  1. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችለውን የዘመነ ግብር የተከከፈለበትን ከሚፈለገው አገልግሎት የተዛመደ የንግድ ሥራ ወይም የአገልግሎት ሥራ ፈቃድ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች ዋጋቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ የፋይናንሻል ፕሮፖዛሉን በተለያየ ፖስታ በማድረግ አንድ ዋና እና አንድ ኮፒ ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ ኦርጅናል እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ ለብቻው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከባለስልጣኑ ዋና መ/ቤት መውሰድ ይችላሉ።
  4. የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሠረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም አቅራቢ ከፍት ነው።
  5. አቅራቢዎች ጨረታውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ገቢ የሚያደርጉት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰአት ድረስ ይሆናል።
  6. ጨረታው በዚያኑ ቀን ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል።
  7. ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
  8. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ መንገድ ብር 40,000.00/ አርባ ሺህ ብር ብቻ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በግዥ መመሪያው ላይ በተፈቀደ አቅራቢው በሚፈልገው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም።
  9. ተጫራቾች በጨረታው ደንብና መመሪያ መሰረት ጨረታውን ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከጨረታው ደንብና መመሪያ ውጭ የሚቀርብ ማንኛውም ጨረታ ተቀባይነት የለውም።
  10.  መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  11.  ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ።

የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን

እቅ/ን/አስ/ደጋፊ የሥራ ሂደት

የፖስታ ሳጥን ቁጥር 404

የስልክ ቁጥር በ0461315012/0932708847/0923690085

ዲላ ኢትዮጵያ

የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን


Tender details

  • Deadline: 2026-10-31
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰአት
  • Bid opening: 2026-10-31 14:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰአት
  • Region: South Ethiopia Regional State
  • Publishing entity: South Ethiopia Roads Authority
  • Bid bond: 40,000.00 ብር ለእያንዳንዱ መንገድ
  • Bid document price: 500.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published on: Addis Zemen (Oct 16, 2026)
  • Posted at: 2026-10-16T08:36:01.000Z
← Back to all tenders