Building Construction

በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር የወረዳ 05 የትምህርት ብልጭታ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሊያሰራው ለፈለገው ጥገና ስራ ላይ የሚሰሩ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ በማወዳደር ለማሰራት ይፈልጋል

Description

የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ተቋ 001/2019 ዓ.ም

በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር የወረዳ 05 የትምህርት ብልጭታ አንደኛና መካከለኛ ደርጃ ትምህርት ቤት ሊያሰራው ለፈለገው ጥገና ስራ ላይ የሚሰሩ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ በማወዳደር ለማሰራት ይፈልጋል። በመሆኑም ለግንባታ አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን፣ የሰው ሃይል በማቅረብ የሚሰሩ በጥቃቅን አነስተኛ ዘርፍ በጥቃቅን አነስተኛ መብቃት ማህበራትን በግል ጨረታ በማወዳደር ለማራት ይፈልጋል።

ተቋራጮች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

ሎት

የስራው አይነት

የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና

ደረጃ

 

የጨረታ ሰነድ መሸጥ የሚጀመርበት ቀን

የጨረታ ማስገቢያ ቀን 

የጨረታ መካፈቻ ቀን

ሎት 1

የወረዳ 05 የትምህርት ብልጭታ አ/መ/ደ/ት/ቤት ጥገና ስራ

ከተደራጁበት ወረዳ የዋስትና ደብዳቤ

 

በጥቃቅን አነስተኛ መብቃት

በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት 2፡30-10፡00 ሰዓት

በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 4፡00 ድረስ ብቻ

በጋዜጣው ከወጣበት በ16ኛው የስራ ቀን 4፡15 ሰዓት ጀምሮ

1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመውሰድ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ህጋዊ ዶክሜንታችሁን ዋናውንና አንድ ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል።

2. በዘርፉ የ2018/19 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የምዝገባ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና ከስራ ክህሎት ቢሮ የታደሰ የዕድገት ደረጃ የምስክር ወረቀት እና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ታክስ ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

3. ከመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የተመዘገቡ ምስክር ወረቀት ያላቸው።

4. ማንኛውም ስራ ተቋራጭ ከአዲስ አበባ ከተማ ግንባታ እና ፍቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን ተመዝግቦ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ሳይዝ በጨረታው መሳተፍ አይችልም።

5. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በአየር ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት 2፡30 እስከ 10፡00 ድረስ ከተራ ቁ 1-4 ከላይ የተጠቀሱትን ማሰረጃዎች ዋናውን (original) እና የማይመለስ ቅጂ (copy) ይዞ በመቅረብ በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ወረዳ 05 የትምህርት ብልጭታ አ/መ/ደ/ት/ቤት በፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 3 ቀርበው ሠነዱን መውሰድ ይችላሉ።

6. ጨረታው የሚከፈተው በ16ኛው የሥራ ቀን በዕለቱ ባለቤቱና ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በጽ/ቤቱ ጠዋት 4፡00 ተዘግቶ በዕለቱ 4፡15 የሚከፈት ይሆናል

7. ማንኛውም ተጫራች የቀረበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማቅረብ ያለበት በቴክኒካል ኦርጂናል ሰነድ ውስጥ ወይም ከፖስታው ውጪ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

8. አሰሪው መ/ቤት አሸናፊው ካሸነፈበት አጠቃላይ የስራ መጠን 20% መጨመርም ሆነ መቀነስ ይቻላል።

9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድን ከማስገባታቸው በፊት የተጫራቾችን መመሪያ (instruction to Bidder)(TB) እንዲያነቡና የግንባታ ሳይቱን እንዲመለከቱ ይመከራል።

10. ተጫራቾች ቴከኒካል ሰነድ አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ፣ ፋይናንሺያል ሰነድ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ በድምሩ ስድስት ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም የታሸገውን ፖስታ በአንድ እናት ፖስታ የድርጅቱን ማህተም እና የሚወዳደሩበትን የስራ ፕሮጀክት አይነት ስም በመጻፍ ታሸጎ መቅረብ ይኖርበታል። እንዲሁም የጨረታው ፋይናንሻል ሰነድ ላይ ያልተፈረመ ሆኖ ስርዝ ድልዝና በፍሉድ የተስተካከለ ዋጋ ከሆነ ሙሉ ለሙሉ ከጨረታው ያሰረዛል። በተጨማሪም በስራ ዝርዝር በሙሉም ሆነ በአንድ የስራ አይነትም ላይ ዋጋ አለመሙላት ከተገኘ ስራውን በነጻ እንደሚሰራ ይወሰዳል።

11.ተጫራቾች የሥራዎችን የዋጋ ዝርዝር እና የጨረታ መወዳደሪያ ላይ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን እና አድራሻቸውን አስፍሮ ማህተም በማድረግ ኢንቨሎፑን በማሸግ ማስታወቂያው በወጣበት በ16ኛው የስራ ቀን በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ወረዳ 05 የትምህርት ብልጭታ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 3 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እሰከ 4፡00 ማስገባት ይኖርባቸዋል።

12. አሸናፊ ተጫራች በስራ ዝርዝር ላይ ከገበያ ዋጋ በጣም ከፍ ያለ እና ዝቅ ያለ ዋጋ ከሞላ (Cost Break Down) ያቀርባል።

13. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የድርጅቱ የስራ ልምድና ማንኛውም በቴክኒካል የተጠየቁት ዶክመንቶችን አሰሪ መ/ቤት ኦርጂናል ዶከመንት ከሰጠው አካል የማጣራት መብት የተጠበቀ ነው።

14. ጨረታውን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው በወጣበት በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡15 ጀምሮ በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 05 የትምህርት ብልጭታ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 3 ይከፈታል። የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት እና ቦታ የሚከፈት ይሆናል።

15. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ደጃች ውቤ በሚገኘው የትምህርት ብልጭታ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፋይናንስ ቢሮ ቁጥ 03 በመቅረብ ወይም 0111266273 /011156 57 06 ደውለው መረዳት ይችላሉ።

አራዳ ክ/ከተማአስተዳደር የወረዳ 05 የትምህርት ብልጭታ አንደኛና መካከለኛ ደርጃ ትምህርት ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-04
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00
  • Bid opening: 2026-11-04 10:15
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡15
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Yetmhirt Bilchita Elementary School
  • Buyer address: በአራዳ ክ/ከተማ በወረዳ 05 ትምህርት ጽ/ቤት አዲስ አበባ ሬስቶራንት አካባቢ ደጃች ውቤ ሰፈር
  • Bid bond: ከተደራጁበት ወረዳ የዋስትና ደብዳቤ
  • Published on: Addis Zemen (Oct 17, 2026)
  • Posted at: 2026-10-17T08:16:23.000Z
← Back to all tenders