Audio Visual, Photography and Filming Service and Equipment
የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የቪዲዮ እና የፎቶ ማለትም “DUAL” የሆነ ካሜራ ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል
Audio Visual, Photography and Filming Service and EquipmentArtEquipment and Accessories
South Ethiopia Regional State
Description
የቪዲዮ እና ካሜራ ግዥ ለመፈጸም የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ደኢመባ ቁጥር 03/2019
የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የቪዲዮ እና የፎቶ ማለትም “DUAL” የሆነ ካሜራ ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል::
በመሆኑም፡-
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን ከሚፈለገው አገልግሎት የተዛመደ የንግድ ሥራ ወይም የአገልግሎት ሥራ ፈቃድ ከሁለት መቶ ሺህ ብር በላይ ላላቸው ግዢዎች የቫት ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ፣ በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆናቸው የምዝገባ ማስረጃ እና በጨረታ ለመሳተፍ ከሚመለከተው የመንግሥት አካል የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳብ የሚያቀርቡበትን የጨረታ ሰነድ የቴክኒክ እና ፋይናንሻሉን አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ በማድረግ ለየብቻው በታሽገ ፖስታ የጨረታ ማስከበሪያው ደግሞ ኦሪጅናልና ኮፒ በተለየ ፖስታ በማድረግ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን፤ አድራሻቸውንና የሚጫረቱበትን የጨረታ ዓይነት በትክክል ማስፈር አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከባለስልጣኑ ዋና ቢሮ ቁጥር --- መውሰድ ይችላሉ፡፡
- አቅራቢዎች ጨረታውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ገቢ የሚያደርጉበት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ድረስ ይሆናል፡፡ ጨረታው በዚያኑ ቀን ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ/ሲፒኦ/ ወይም በባንክ ዋስትና ወይም ከኢንሹራንስ ዋስትና በቀር በግዥ መመሪያው ላይ ባሉ አማራጮች በፈለጉት ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ አይችሉም፡፡
- ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ይሰረዛሉ፡፡ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ይወረሳሉ፡፡ ለወደፊቱም መ/ቤቱ በሚያወጣው የግዥ ጨረታ እንዳይሳተፉ ይደረጋል፡
- ተጫራቾች ያቀረቡት ዋጋ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ለ45 ቀናት ፀንቶ መቆየት አለበት፡፡
- ተጫራች የጨረታው አሸናፊ ድርጅት መሆኑ ከተገለፀለት አምስት /5/ ቀናት ውስጥ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና Performance Bond 10% በባንክ ጋራንቲ ወይም በሲፒኦ በማቅረብ ውል መፈረም ይኖርበታል፤ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ውል ለመፈረም ፈቃደኛ ያልሆነ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ይወረሳል፡፡
ተጫራቾች በእንግሊዘኛ የተጻፈውን የቴክኒክ ዝርዝር መግለጫ በሚጠይቀው መሠረት መሙላት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህንን ያልሞሉት የቴክኒክ ዝርዝር መግለጫ እንዳልቀረበ ተቆጥሮ የማቅረቢያ ሰነዱ ውድቅ ይደረጋል፡፡ ተጫራቾች ከዚህ በታች በቀረበው መሠረት፡-
|
ተ.ቁ |
የዕቃው ዓይነት |
Qty |
የጨረታ ማስከበሪያ |
|
1 |
DUAL CAMERA |
01 |
25,000.00 |
ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡-
የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን
ግዥና ንብረት አስተዳደር ኬዝ ቲም
የስልክ ቁጥር 0461315012/0923690085/0911041447
ዲላ ኢትዮጵያ
የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን
Tender details
- Deadline: 2026-11-02
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-02 14:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
- Region: South Ethiopia Regional State
- Publishing entity: South Ethiopia Roads Authority
- Bid bond: 25,000.00 ብር
- Bid document price: 400.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 18, 2026)
- Posted at: 2026-10-19T10:33:08.000Z
- Source: Qelal Tenders