Land Lease & Real Estate

የደብረ ታቦር ከተማ መሬት መምረያ ለመኖረያ አገልግሎት የሚውሉ ቦታዎችን በሊዝ በጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል

Description

የመሬት ሊዝ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የደብረ ታቦር ከተማ መሬት መምረያ የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነገገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 መሰረት በ2019 በጀት ዓመት 1ኛ ዙር 20 ለመኖረያ አገልግሎት የሚውሉ ቦታዎችን በሊዝ በጨረታ ለተጫራቾች ማስተሳሰፍ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም፦

  1. ጨረታው በጋዜጣ ጥቅምት 09/2019 እስከ ጥቅምት 20/2019 ዓ/ም ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀን በጋዜጣ ይውላል፡፡ ስለዚህ መጫረት የሚፈለጉ ሁሉ የጨረታ ሰነዱን የደ/ታቦር ከተማ መሬት መምሪያ ቢሮ ቁጥር 22 ድረስ በመምጣት እና በመመዝገብ የማይመሰስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ሠነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
  2.  የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ቀን ጥቅምት 09/2019 እስከ ጥቅምት 20/2019 ዓ/ም ድረስ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በመንግስት የሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 የደ/ታቦር ከተማ መ ሬት መምሪያ ግቢ ውስ ጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳ ጥን ውስጥ ይሆናል፡፡
  3. ጨረታው የሚዘጋው ጥቅምት 20/2019 ዓ/ም በ11፡00 ይሆናል፡፡
  4. ጨረታው የሚከፈተው ጥቅምት 21/2019 ዓ/ም በ3፡00 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የደ/ታቦር ከተማ መሬት መምሪያ ግቢ ውስጥ ነው፡፡
  5. ሁሉም ተጫራቾች በፖስታ አሽገው ማስገባት ያለባቸው የሀሳብና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ፣ በባንክ የተረጋገጠ የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ (ሲፒኦ) ለድርጅት 15 በመቶ እና ለመኖሪያ 20 በመቶ፣ የተከፈለበት፣ ኦርጅናል ዋናውን ሰነድ የገዙበት ደረሰኝ ናቸው፡፡
  6. የጨረታ ቦታዎችን ብዛት እና ሳይት ኘላን በውስጥ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በተለጠፈው መመልከት ይችላሉ፡፡
  7. መስሪያ ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የደብረ ታቦር ከተማ መሬት መምሪያ


Tender details

  • Deadline: 2026-10-30
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid opening: 2026-10-31 09:00
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: የደብረ ታቦር ከተማ መሬት መምሪያ
  • Bid bond: ለድርጅት 15 በመቶ እና ለመኖሪያ 20 በመቶ
  • Bid document price: 500 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Be'kur (Oct 19, 2026)
  • Posted at: 2026-10-19T14:16:33.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders