Hotel Service Provision
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ጽ/ቤት በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ለጽ/ቤቱ የሚያስፈልጉ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ በማወዳደር መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ጽ/ቤት በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ለጽ/ቤቱ የሚያስፈልጉ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የጨረታ ሎቶች ለሁለተኛ ጊዜ በግልጽ ጨረታ በማወዳደር መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1. የሆቴል መስተንግዶ አገልግሎት
- ሎት 2. የዲኮር ግብዓቶች እና ሌሎች አገልግሎቶች በኪራይ
- ሎት 3. የፕሮቶኮል ልብስ
- ሎት 4. የተፈጥሮ ውሃ
- ሎት 5. የባህል ልብስ
- ሎት 6. የደንብ ልብስ
በጨረታ ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 400 በመክፈል ሰነዱን ከግዢ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 105 1ኛ ፎቅ መግዛት ይቻላል።
1. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት 1000011113625 አዲስ አበባ ከተማ ም/ቤት ከአጠቃላይ ዋጋ CPO 2% በማስያዝ የባንክ እስሊፑን ይዘው መምጣት ይኖርባቸዋል።
2. የጨረታው አሸናፊ የውል ማስከበሪያ 10% (አሥር በመቶ) CPO በማስያዝ ከመ/ቤቱ ጋር ውል ይፈራረማል።
3. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት መግዛት ይችላሉ።
4. የጨረታ ሰነድ በየሎቱ ዋናውና ኮፒውን ለየብቻው ተፈርሞበት በየገፁ ማህተም በማድረግ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. ተጫራቾች የሚሞሉት የአንዱ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ከነቫቱ መሆን አለበት ይህሳይሆን ሲቀር መ/ቤቱ ቫት እንደተካተተ አድርጎ ይወስዳል።
6. ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም።
7. በሎት 1 ሜኑ ሎት 3፤5፤ ሎት 6 የምትወዳደሩባቸውን ናሙና መቅረብ አለበት።
8. ተወዳዳሪዎች ለተመሳሳይ አገልግሎት ተመሳሳይ ዋጋ ካቀረቡ በዕጣ የሚለይ ይሆናል።
9. ጨረታዉ ከተከፈተ በኋላ የሚቀርብ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
10. በጨረታው በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት ተዘግቶ ከቀኑ በ4፡00 ሰዓት ተወዳዳሪዎች በአካል ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
12. አሸናፊ ድርጅት ውል ከተዋዋለ በኋላ ዋጋ መጨመርና መቀነስ የማይቻል መሆኑ፤
13. መ/ቤቱ ከተገኘው ዋጋ ሳይቀይር እስከ 25% የእቃውን ወይም አገልግሎቱን መቀነስ ወይም መጨመር የሚችል መሆኑን።
14. በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ
የሚጠበቁ ቅድመ ሁኔታዎች፤
1. የዘመኑ ግብር የተከፈለበት የምሥክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና ምዝገባ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
3. በሎት 1 የሚወዳደሩ በሥራ ዘርፉለመሰማራታቸው የብቃት ማረጋገጫ ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. የቫት ተመዝጋቢ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖባቸዋል።
ለበለጠ መረጃ
አድራሻ፡-ከሳንቺስ ልማት ባንክ ጀርባ
ስልክ ቁጥር ፡-09 13 04 35 09 ይደውሉ።
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-30
- Bid closing time: 09:30
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ3፡30
- Bid opening: 2026-10-30 10:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Addis Ababa City Council Office
- Buyer's registered address: ሪቼ መስከረም ማዞሪያ
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 400 (አራት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Oct 19, 2026)
- Posted at: 2026-10-19T14:38:19.000Z
- Source: Qelal Tenders