Vehicle

በአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ የሰሜን ሸዋ ገጠር መንገዶች ጥገና ጽ/ቤት 29 ሰው የመጫን አቅም ያለው የሠራተኞች ሰርቨስ መኪና አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ተሸከርካሪ ኪራይ አገልግሎት ግዥ
የጨረታ ቁጥር፡- 01/2019 ዓ.ም

በአማራ ገጠር መንገዶች ከንስትራክሽን ኤጀንሲ የሰሜን ሸዋ ገጠር መንገዶች ጥገና ጽ/ቤት ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት 29 ሰው የመጫን አቅም ያለው የሠራተኞች ሰርቨስ መኪና አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም የሚከተሉትን መመሪያዎች መሠረት በማድረግ በጨረታዉ እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፤
  3. ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን እና ታክስ ክሊራንስ የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤ የሰርቪስ መኪና መወዳደር ይችላሉ
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚቀርበው ተሽከርካሪ የፈረስ ጉልበቱ የስሪት ዘመኑ እና ሌሎች በጨረታ ሰነዱ የተገለፁትን መስፈርቶች አሟልተዉ መቅረብ አለባቸው፡፡
  6. የኪሎ ሜትር እና የነዳጅ ቆጣሪው በትክክል የሚሠራ መሆን አለበት፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሰርቪስ መኪና 20,000.00 በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም ጨረታ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ28 /ሃያ ስምንት/ ቀናት የሚቆይ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ብሄራዊ ባንክ እውቅና ከሰጣቸው ባንኮች ብቻ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ሰሜን ሸዋ ገጠር መንገዶች ጥገና ጽ/ቤት ደ/ብርሃን በአካል በመገኘት መግዛት ይችላሉ፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሂሳቡን ፋይናንሻልንና ቴክኒካሉን ሰነዳቸውን በአግባቡ በመጠረዝ በፖስታ በማሸግ የተሟላ አድራሻ በመፃፍ ተዘጋጅቶ ከግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለ10 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ውሎ በ11ኛው ቀን 8፡30 ሰአት ላይ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት ይከፈታል፡፡
  10. የዋጋ መሙያ ቅፁ ላይ ስርዝ ድልዝ እና ፍቀት ካለው ፊርማ ያለው ቢሆንም ስርዝ ድልዝ ከጨረታ ውድድር ውጪ ይደረጋል፡
  11. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በፋክስ ቁጥር 011-681-38-85 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 0913 189 073 ወይም 0987 634 263 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የሰሜን ሸዋ ገጠር መንገዶች ጥገና ጽ / ቤት
ደ/ብርሃን


Tender details

  • Deadline: 2026-10-28
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለ10 ተከታታይ ቀናት
  • Bid opening: 2026-10-29 14:30
  • Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለ10 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ውሎ በ11ኛው ቀን 8፡30 ሰአት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: North Shoa Rural Road Maintenance Office
  • Bid bond: 20,000.00 ብር
  • Bid document price: 300.00 (ሶስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Oct 19, 2026)
  • Posted at: 2026-10-19T14:48:25.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders