Construction Machinery and Equipment
የሸኖ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ለሸኖ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና ለተለያዩ መ/ቤቶች የተለያዩ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
ማስታወቂያ ጨረታ
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- ግ/ጨ/ቁ 02/2019
የሸኖ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በኦሮሚያ የስራ ዕድል ፈጠራ እና ሙያ ቢሮ ለሸኖ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና ለተለያዩ መ/ቤቶች የተለያዩ፦
- Construction material
- ICT & Electronics Material
- Automotive material
- Metal and welding material
- Electrical electronics
- Material for BEI
- የተለያዩ የህትመት ዉጤቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡
ስለዚህ በየስራ ዘርፉ የዘመኑን ግብር የከፈላችሁ፤ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላችሁ፤የተጨማሪ እሴት ታክስ WAT 15% ተመዝጋቢ የሆናችሁ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN ያላችሁ እና በአቅራቢዎች ዝርዝር ዉስጥ የተመዘገቡ ለመሆናቸዉ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በሸኖ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በግንባር በመቅረብ ዝርዝር መጠይቆችን የያዘውን ሰነድ በማይመለስ በብር 800 በካሽ መግዛት ይችላሉ።
ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ በዝርዝር የተመለከተውን የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና በካሽ ወይም ሲፒኦ CPO ማስያዝ አለባቸው።
ተጫራቾች በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ በመያዝ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ በ16ኛው ቀን እስከ 8:00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዚሁ እለት በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮች በተገኙበት ይከፈታል።
ማሳሰቢያ፦
ጨረታውን ያሸነፈ ድርጅት ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ውሉን ፈጽሞ እቃዎችን የማስገባት ግዴታ አለበት።
መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ (አማራጭ) ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ በሚወስደው መንገድ 78 ኪሎ ሜትር ሸኖ ከተማ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- ዐ9 10 09 33 62 በመደወል ጠይቆ መረዳት ይቻላል።
በኦሮሚያ ክልል የሸኖ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-11-05
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን እስከ 8:00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-05 14:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን እስከ 8:30 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: Sheno City Finance and Economic Bureau
- Bid document price: 800.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 19, 2026)
- Posted at: 2026-10-19T15:30:25.000Z
- Source: Qelal Tenders