Building Construction
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር አዲስ ታንከር መግዛት እንዲሁም የታንከር ቦታን የመቀየር እና ለአፍሪካ ህንጻ የሴፕቲክ ታንክ ስላብ ስራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ ለመፈጸም ይፈልጋል
Description
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ
Commercial Nominees PLC
የጨረታ ማስታወቂያ
CN/NCB/11/19
የድርጅታችን ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር አፍሪካ ህብረት ስሚገኘው ህንጻ፡-
- ሎት 1፡- አዲስ ታንከር መግዛት እንዲሁም የታንከር ቦታን የመቀየር
- ሎት 2፡- ለአፍሪካ ህንጻ የሴፕቲክ ታንክ ስላብ ስራ (በድጋሚየወጣ)
መስራት የሚችሉ ከደረጃ 5 በላይ ያሉ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ ለመፈጸም ይፈልጋል:: በመሆኑም ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ በጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ መሆኑን የሚገልጽ ደብዳቤ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡትን ማስረጃ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ እና የዕቃው ወይም የአገልግሎቱ ዝርዝር መግለጫ በተለየ በሰም በታሸገ ፖስታ እንዲሁም ዕቃዎቹን የምታቀርቡባቸውን ዋጋ በተለየ በሰም በታሸገ ሁለተኛ ፖስታ በማድረግ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል::
የጨረታ ዶክመንቱን ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ የግዢ ዋና ክፍል ብር 100.00 በመክፈል ከሰኞ እስከ ዓርብ (ጠዋት 2፡00-6፡00 እንዲሁም ከሠዓት 7፡00-10፡30) እና ቅዳሜ ግማሽ ቀን (ጠዋት 2፡00-6፡00) ማግኘት ይቻላል:: የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት1 ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ) እንዲሁም ለሎት2 ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ. ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከመጫረቻ ዶክመንት ጋር መቅረብ ይኖርበታል::
ተጫራቾች የመጫረቻ ዶክመንታቸውን ከላይ በተጠቀሰው አድራሻና የሥራ ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ጥቅምት 24 ቀን 2019 ዓ.ም 4፡00 ጠዋት ድረስ ማስገባት ይችላሉ:: ጨረታው በዚሁ ዕለት በ 4፡30 ጠዋት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል:: ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ያላሟላ ተጫራች ያለተጨማሪ ማስታወቂያ ከውድድሩ ዉጪ ይደረጋል::
ድርጅቱ ጨረታውን በከፊስም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ
ቦሌ መንገድ ደንበስ የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ
ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ
ስልክ ቁጥር 011-1-569992
አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
Tender details
- Deadline: 2026-11-03
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-11-03 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Commercial Nominees P.L.C.
- Buyer TIN: 0000958158
- Buyer's registered address: ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published on: Reporter (Oct 18, 2026)
- Posted at: 2026-10-20T08:18:51.000Z
- Buyer website: https://commercialnominees.com/
- Source: Qelal Tenders