Construction Machinery and Equipment
የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ የማጠናከሪያ ብረት፣ የድልድይ ቤሪንግ እና ጋቢዮን ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Construction Machinery and EquipmentConstruction and Water WorksSteel Raw Materials and Products
Amhara
Description
ብሄራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር-02/2019
የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ለሚያከናውናቸው
- የመንገድ ግንባታ እና ጥገና አገልግሎት የሚውል የማጠናከሪያ ብረት፣
- የድልድይ ቤሪንግ እና ጋቢዮን ግዥ
በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ለውድድር ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN ያላቸው፣
- ተጫራቾች የሚጠበቅባቸውን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው ::
- የግዥው መጠን ከብር 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ / VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- የሚገዙ የማጠናከሪያ ብረት ፣ የድልድይ ቤሪንግ እና ጋቢዮን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /specification/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/በመ/ቤቱ አካውንት ቁጥር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000013197966 በመክፈል የባንክ ዲፖዚት ስሊፕ በመያዝከገንዘብ ያዥ ከፍል ቢሮ ቁጥር 09 ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ከ10/o2/2019 ዓ.ም ጀምሮእስከ ቀን 20 / 02/2019 ዓ.ም ማግኘት ይቻላል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የማጫረቻ ሰነዱን ማለትም ዋናና ኮፒ (Original and Copy) በማለት በአንድ ኢንቨሎፕ በጥንቃቄ በማሸግ በኤጀንሲው ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 03 ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት /በአየር ላይ ከዋለበት/ ቀንከ10/02/2019 ዓ ም ጀምሮ እስከ ቀን 20/02/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ዋጋ ሲሞላ ቫትና ሌሎች ታክስ እንዲሁም የትራንስፖርት ዋጋን ጨምሮ መሆን አለበት ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው፣ ሆኖም የጠቅላላ ዋጋው 1% ከብር 2,000,000.00 /ሁለት ሚሊዮን ብር/ የሚበልጥ ከሆነ 2,000,000,00 /ሁለት ሚሊዮን ብር/ ብቻ ማስያዝ ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኤጀንሲው ዋና መ/ቤት ግዥ ኦፊሰሮችቢሮ በቀን 20-/02/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን 8፡30 ግዥ ኢፊሰር ቢሮ ቁጥር 03 ይከፈታል፡
- የጨረታው መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በእያንዳንዱ የዋጋ መሙያ ገፅ ላይ ፊርማና መህተም ማድረግ አለባቸው፡፡ በተጨማሪም በዋጋ መሙያው ላይ ስርስ ድልዝና በፍሉድ የጠፋ ከውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡
- በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከኤጀንሲው ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 03 በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058-222-1100 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር058-322-5155 /058-222-1107 በመደወል ወይም በኤጀንሲው ድህረ ገጽ -www.arrca.gov.et ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ኤጀንሲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
(ባህር ዳር)
አማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገጠር መንገዶች
ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ
Tender details
- Deadline: 2026-10-30
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-10-30 14:30
- Region: Amhara
- Publishing entity: ANRS Rural Road Construction Agency
- Buyer's registered address: ባህርዳር ከተማ ቀበሌ 13
- Bid bond: 1%
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 20, 2026)
- Posted at: 2026-10-20T15:52:21.000Z
- Source: Qelal Tenders