Pharmaceutical Products

የጅማ ዩኒቨርስቲ ገቢ ማመንጫና ኢንቨስትመንት ዳይሬክቶሬት ለጅማ ዩኒቨርስቲ ሞዴል ኮሚኒቲ ፋርማሲ አገልግሎት የሚውሉ መድኃኒቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይጋብዛል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጅማ ዩኒቨርስቲ ገቢ ማመንጫና ኢንቨስትመንት ዳይሬክቶሬት ለጅማ ዩኒቨርስቲ ሞዴል ኮሚኒቲ ፋርማሲ አገልግሎት የሚዉሉ መድኃኒቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት፡1  የመድኃኒት ግዥ

በዚሁ መሠረት በጨረታው መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ሕጋዊ ተጫራች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል።

  1. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት የተለያዩ የመድሐኒቶች አቅርቦት ጋር አግባብነት ያለው በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር የአቅራቢነት የምዝገባ የምስከር ወረቀት፣ ከገቢዎች ሚኒስቴር የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት እና ወቅታዊ የግብር ግዴታዎችን እየተወጡ ያሉና በጨረታ ተካፋይ ለመሆን እንዲችሉ የሚገልጽ የሀገር ውስጥ ገቢ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ ዋጋ ሞልተው ሲመልሱ ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 (ሀምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ CPO ወይም የባንክ ዋስትና (Bid bond) እንዲሁም በማይክሮ የተደራጁ ከሆነ ካደራጃቸዉ ከጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ የጨረታ ዋስትና በጅማ ዩኒቨርሲቲ ሞዴል ኮሚኒቲ ፋርማሲ ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች ለአሸነፉባቸው የተለያዩ የመድሐኒቶች አቅርቦቱን የሚፈጽሙት በራሳቸው የትራንስፖርት ወጪ በጅማ ዩኒቨርሲቲ ሞዴል ኮሚኒቲ ፋርማሲ ዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ በማቅረብ ነው።
  4. ተጫራቾች ማናቸውንም የመንግስት ታክስና የግብር ግዴታዎችን በሚያቀርቡት ያንዳንዱ የመወዳደሪያ ነጠላ ዋጋ ውስጥ አካተው ማቅረብ አለባቸው።
  5. ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ተጫራች በጅማ ዩኒቨርሲቲ ሞዴል ኮሚኒቲ ፋርማሲ ቢሮ ወይም የጅማ ዩኒቨርሲቲ ጉዳይ ማስፈፀሚያ ጽ/ቤት (ልደታ ባልቻ ሆስፒታል ጀርባ ከብስራት ሆቴል 100 ኪሜ ከፍ) ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሠዓት በግንባር መረጃዎችን ይዞ በመቅረብ የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር በመክፈል የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ።

የጨረታው ሠነድ የሚዘጋውና የሚከፈተው

የጨረታ ሠነድ የመድሐኒት ግዥ እስከ ጥቅምት 27 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ አድርገው በጅማ ከተማ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ገቢ ማመኑና ኢንቨስትመንት ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው የሚከፈተዉ በዛዉ ዕለት ጥቅምት 27 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:15 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጅማ ዩኒቨርሲቲ ገቢ ማመንጫና ኢንቨስትመንት ዳይሬክቶሬት ቢሮ የሚከፈት ይሆናል ።

የበለጠ መረጃ ቢያስፈልግዎት በስልክ ቁጥር 0471 116912 ወይም 0111550621 አዲስ አበባ መጠየቅ ይችላሉ።

ዩኒቨርስቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ሞዴል ፋርማሲ


Tender details

  • Deadline: 2026-11-06
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-11-06 10:15
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Jimma University
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 21, 2026)
  • Posted at: 2026-10-21T10:33:57.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders