Carpets and Curtains

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የደቡብ አዲስ አበባ ሪጅን የመስኮት መጋረጃ (ስራና ገጠማ) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር ደ/አ/አ/ሪ/ብ/ግ/ጨ/002/2019(NCB)

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የደቡብ አዲስ አበባ ሪጅን 6ኛ እስከ 8ኛ ፎቅ ያሉትን ቢሮዎች መጋረጃ ከዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

ተቁ

የእቃው አይነት

የመዝጊያ ቀንና ሰአት

የመክፈቻ ቀንና ሰአት

የጨረታ ማስከበሪያ

1

የመስኮት መጋረጃ (ስራና ገጠማ)

ጥቅምት 26 ቀን 2019 ከቀኑ 8፡00

ጥቅምት 26 ቀን 2019 ከቀኑ 8፡30

50,000/ሀምሳ ሺህ ብር/

 

  1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ የሚያቀርቡና በመስኩ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው ፤የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው::
  2. የጨረታ ሰነዱን ጥቅምት 13 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000173799946 (EEU-South Addis Ababa Region Customer Contribution) በማስገባትና ደረሰኙን ይዞ በመምጣት የኢ.ኤ.አ. የደቡብ አዲስ አበባ ሪጅን ከቀድሞ ግሎባል ሆቴል ፊት ለፊት ማከቤንዝ ህንጻ 6ኛ ፎቅ ላይ መግዛት ይችላሉ፡፡
  3.  ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 (ሀምሳ ሺህ ብር) በባንከ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም የዋስትና ጊዜው ከሚያበቃበት ቀን በኋላ 28 ቀን ተጨማሪ ጊዜ ያለውን የባንክ ዋስትና (Bank Guarantee) በኢ.ኤ.አ.ደቡብ አዲስ አበባ ሪጅን ስም ተዘጋጅቶ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው::
  4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታ ቁጥር ደ/አ/አ/ሪ/ብ/ግ/ጨ/0002/2019 (NCB) የሚል ምልክት በማድረግ እና የጨረታ ቁጥሩን በመፃፍ እስከ ጥቅምት 26 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ በኢ.ኤ.አ. የደቡብ አዲስ አበባ ሪጅን ከቀድሞ ግሎባል ሆቴል ፊትለፊት ማከቤንዝ ህንጻ 6ኛ ፎቅ ላይ በመምጣት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት /ባይገኙም/ ጥቅምት 26 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ላይ ይከፈታል፡፡
  6. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ከሰዓት 7፡00-11፡00 እና ቅዳሜ ጠዋት 2፡00 – 6፡00 ሰዓት ማግኘት ይችላሉ ፡፡
  7. የፕሮግራም ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፍል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ::
  8. ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር +251-114705377 መደወል ይችላሉ፡፡

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት

የደቡብ አዲስ አበባ ሪጅን


Tender details

  • Deadline: 2026-11-05
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-11-05 14:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Electric Utility
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 400.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 24, 2026)
  • Posted at: 2026-10-24T09:33:27.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders