Building Construction
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በስልጤ ዞን የዓለም ገበያ ከተማ አስተደዳር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለሚያስገነባቸው 04 ሎቶች የኮሪዶር Corridor/ ግንባታ በመስኩ የተሰማሩ ተቋራጮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በስልጤ ዞን የዓለም ገበያ ከተማ አስተደዳር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለሚያስገነባቸው 04 ሎቶች የኮሪዶር Corridor/ ግንባታ በመስኩ የተሰማሩ ተቋራጮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል። ስለሆነም ደረጃቸው G.C-6/B.C 6 እና ከዛ በላይ የሆኑ፤
- የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፊኬት የሚያቀርብ፤
- የታደሰ የንግድ ፈቃድና የስራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የኮንስትራክሽንና ከተማ ልማት ሚኒስተር የዘመኑን የምዝገባ ሰርተፊኬት የሚያቀርቡ፤
- የጨረታ ዋስትና 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ለአንድ ሎት ብቻ ማስያዝ የሚችሉ፤
- የመስራት አቅም እንዳላቸው የሚገልፅ የወቅቱን የባንክ እስቴትመንት እና የስራ ልምድ ብቃት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የኦዲት ሪፖርት እና የድርጅቱን አወቃቀርና ከዚህ በፊት የሰሯቸውን ስራዎች የሚገልፅ የስራ ልምድ ማቅረብ የሚችሉ ተቋራጮች ሰነዱን የዓለም ገበያ ከተማ አስተደዳር ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 በመቅረብ ለአንድ ሎት ሰነድ የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን የጨረታ ሰነዱን ፋይናንሽያል ዶክመንቱን በሚገባ በመሙላት አንድ ኦርጂናል እና ሁለት ኮፒ ለየብቻ፣ ቴክኒካል ዶክመንቱን አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት በኋላ ባለው የስራ ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ ዓለም ገበያ ከተማ አስተደዳር ፋይናንስ ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ሳጥኑ በዚሁ ዕለት 8፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
ማሳሰቢያ፡-
- ተጫራቾች ያቀረቡት የጨረታ ዋስትና ከተጠየቀው ዋጋ አንሶ ከተገኘ ከጨረታው ይሰረዛሉ።
- አንድ ተጫራች ከሁለት በላይ የጨረታ ሰነድ ሞልቶ ማቅረብ አይችልም።
- አንድ ተጫራች ሁለት የጨረታ ሰነድ ሞልቶ ማቅረብ ቢፈልግ ቴክኒካል ዶክመንት አንድ ብቻ ለሁለቱም ሎቶች ማቅረብ ይቻላል። ፋይናንሽያል ዶክመንት ግን ለየብቻ መሆን አለበት።
- የተወዳዳሪ ተቋራጮች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታ መክፈቻ ቀኑን አይለውጠውም።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ- በስልክ ቁጥሮች 09 08 19 14 58 ወይም 09 12 95 68 37 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የዓለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-11-16
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት በኋላ ባለው የስራ ቀን 8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-16 14:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት በኋላ ባለው የስራ ቀን 8፡30 ሰዓት
- Region: Central Ethiopia
- Publishing entity: ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የዓለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
- Bid bond: 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ለአንድ ሎት ብቻ
- Bid document price: 400.00 /አራት መቶ ብር/
- Published on: Addis Zemen (Oct 25, 2026)
- Posted at: 2026-10-26T08:28:16.000Z
- Source: Qelal Tenders