Food Items and Drinks
ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ የተለያዩ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ በወሊድ ወቅት ችግር የሚገጥማቸውን እናቶች ከስድሳ አመታት በላይ የነፃ ሕክምና እየሰጠ የሚገኝ በጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን፣ ከነፃ ሕክምናው በተጨማሪ በሐምሊን አዋለጅ ነርሶች ት/ቤት በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ፣ እንዲሁም በቡራዩ ልዩ ዘን በሚገኘው የደስታ መንደር መልሶ ማቋቋም ማዕክል፡ በምንሰጠው ሕክምና ለዳኑና ተጨማሪ የቅርብ ክትትል ለሚያስፈልጋቸው እናቶች የራስ አገዝ የሙያ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።
በዚሁም መሠረት ሐምሊን ፊስቱላ አትዮጵያ ቀጥሎ በተዘረዘሩት ምድቦች ግዢ በሚፈፅምባቸው ልዩ ልዩ መገልገያዎች እና አገልግሎቶች ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶችን በዚህ ማስታወቂያ ይጋብዛል።
ምድብ ሀ፡- በአዲስ አበባ ፊስቱላ ሆስፒታል ተኝተው ለሚታከሙ ህሙማን እና በሐምሊን አዋላጅ ነርሶች ት/ቤት ስልጠናቸውን ለሚከታተሉ ተማሪዎች አገልግሎት የሚውሉ የደረቅ ምግብ እና የባልትና ውጤቶች አቅርቦት የማይመለስ የጨረታ ሰነድ መግዣ ብር 400.00/አራት መቶ ብር ብቻ/፣
ምድብ ለ፡- ለድርጅቱ አገልግሎት የሚውሉ የደረቅ እና እሽግ ሳሙና/HARD SOAP & POWDERED DETERGENT/ ግዢ፤ የማይመለስ የጨረታ ሰነድ መግዣ ብር 300.00/ሦስት መቶ ብር ብቻ/፤
ምድብ ሐ፡- ድርጅታችን ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያን የሚገልፅ ሁለት የማስተዋወቂያ ሰሌዳዎች/DIGITAL SGNAGE ሥራ እና ተከላ፣ የማይመለስ የጨረታ ሰነድ መግዣ ብር 300.00/ሦስት መቶ ብር ብቻ/፤
ምድብ መ፡- በሐምሊን የአዋልጅ ነርሶች ት/ቤት የማስተማሪያ ክፍል/ECTURE HALL ለሚገጠም ኦዲዮ- ቪዥዋል ስክሪን የሚያገለግል በቂ አቅም ያለው የብረት ፍሬም ተከላ NVIDEO WALL STRUCTURAL ABBAY/፤ የማይመለስ የጨረታ ሰነድ መግዣ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር ብቻ/፤
ምድብ ሠ፡- በባህርዳር የሐምሊን ፊስቱላ ማዕከል ለሚካሄደው ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ እና ከድርጅቱ የውሃ ሥርጭት መስመር ጋር የማገናኘት ሥራ፤ የማይመለስ የጨረታ ሰነድ መግዣ ብር 400.00/አራት መቶ ብር ብቻ/፤
ምድብ ረ፡- የድርጅታችን ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ አጋር ከሆኑ የመንግስት ጤና ተቋማት ጋር በጋራ እየተተገበረ ላለው የፕሮጀክት ዜሮ አገልግሎት የሚውሉ ስድስት/06/ የሞተር ሳይክሎች ግዢ፤ የማይመለስ የጨረታ ሰነድ መግዣ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር ብቻ/፤
ምድብ ሰ፦ በደስታ መንደር የመልሶ ማቋቋሚያ ማዕከል ግቢ ውስጥ ያለውን የግጦሽ ሳር አጭደው ድርጅታችን በሚፈልገው መልኩ በቦንዳ አስረው የሚያስረክቡ ድርጅቶች፤ የሰነድ ግዢ የለውም!
ምድብ ሸ፡- በደስታ መንደር መልሶ ማቋቋሚያ ማዕከል የሚገኙ እና በሰባት/07/ ምድቦች የተለዩ፣ አገልግሎት ላይ ውለው የሚወገዱ ልዩ ልዩ መሣሪያዎችን እና የመኪና ጎማዎች ሽያጭ፧ የማይመለስ የጨረታ ሰነድ መግዣ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር ብቻ/።
ተጫራቾች ከላይ ለተዘረዘሩት ለእያንዳንዳቸው ምድቦች የተዘጋጁትን ሰነዶች በየምድቦቹ አንፃር የተገለፀውን የሰነድ ክፍያ በመፈፀም ከሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ የፋይናንስ ክፍል መውሰድ ይችላሉ።
የምድብ ሀ፤ ለ፤ መ፤ ረ ፡ እና ስ ጨረታ እስከ ማክሰኞ ጥቅምት 24፣ 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰአት ድረስ የሚቆይ ሲሆን፣ ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማብቂያው ቀን (ጥቅምት 24፣ 2018 ዓ.ም) ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል፤
የምድብ ሐ፧ ሠ እና ሽ ጨረታ እስከ ኅዳር 1፣ 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰአት ድረስ የሚቆይ ሲሆን፣ ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማብቂያው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል፤
ከላይ የተዘረዘሩትን የጨረታ ምድቦች በከፊል ወይንም በሙሉ ለመሰረዝ ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ
ስልክ ቁጥር +251-11 371 6544/45/46-የውስጥ መስመሮች፡ 139/182፤ በተጨማሪም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቹ ላይ በተገለፁት የስልክ ቁጥሮች ደውለው የሚያስፈልጋቸውን ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ
Tender details
- Deadline: 2026-11-10
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-11-10 14:00
- Bid opening (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Hamlin Fistula Ethiopia
- Buyer's registered address: Kolfe Keranyo Sub city woreda 09, House number 920 Betel Hospital Street behind Augusta Shirt Factory
- Published on: Reporter (Oct 25, 2026)
- Posted at: 2026-10-26T10:06:34.000Z
- Source: Qelal Tenders