Pharmaceutical Products
በደቡ/ምዕ/ኢትጵያ ህ/ክ/መ/ በካፋ ዞን አዲዮ ወረዳ ፋይ/ጽ/ቤት 2019 በጀት ዓመት ለግብርና አካ/ጥበቃ አየር ንብረት ለውጥ እና ህ/ስራ ጽ/ቤት የሚውል የእንስሳት መድሃኒት እና የተለያዩ የእንስሳት ህክምና መገልገያ ቁሳቁስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የተቋሙ ስም በደቡ/ምዕ/ኢትጵያ ህ/ክ/መ/ በካፋ ዞን አዲዮ ወረዳ ፋይ/ጽ/ቤት 2019 በጀት ዓመት ለግብርና አካ/ጥበቃ አየር ንብረት ለውጥ እና ህ/ስራ ጽ/ቤት የሚውል
- ሎቲ 1፡- የእንስሳት መድሃኒት
- ሎቲ 2፡- የተለያዩ የእንስሳት ህክምና መገልገያ ቁሳቁስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት፡ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።
1. በዘመኑ ተጫራቾች ሥራን ለማከናወን የሚያስችል የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለውና በሀገርቱና በክልሉ የግብር አዋጅ በተደነገገው መሠረት የግብርና የታክስ ግደታውን የተወጣ ፎቶ ኮፒዎችን አያይዞ ማቅረብ የሚችል/የሚትችል/።
2. ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችል/የሚትችል/።
3. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 400 ብር/አራት መቶ ብር/በመክፈል ከግዥና ንብረት አስ/ር ሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 02 በአካል ቀርበው መግዛት ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾቹ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት ዕቃ ከጠቅላላ ዋጋ 3% በባንክ በተረጋገጠው ሲፕኦ በአዲዮ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም አዘጋጅተው ማቅረብ ይኖርበታል።
5. ተጫራቾቹ የጨረታመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በስም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማሸግ ዋውንና ኮፒውን ስልጣን ባለው አካል ተፈርሞ ማህተም ተደርገው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
6. ጨረታውን በ16ኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽገው በዕለቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ቢሮ ቁጥር 02 ይከፈታል፤ ሆኖም ግን 16ኛዉ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ ሥራ ቀን ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾቹና ህጋዊ ወክሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን የተጫራቾቹ ወይም ወክሎቻቸው ያለመገኘት የጨረታውን አከፋፈት አያስተጓጉልም።
7. ተጫራቾቹ የሚያቀርቡት ዋጋ ቫቲን ማካተቱን እና አለማካተቱን መግለጽ ይኖርባቸዋል፤ሆኖም ግን ተጫራቾቹ ያቀረቡት ዋጋ ቫቲን ስለማካተቱንና አለማካተቱን በግልጽ ያመላከቱ ሆነ የቀረበው ዋጋ ቫቲን እንዳካተተ ተደርገው ይወሰዳል።
8. ተጫራቾቹ የፋይነሻል እና የቴክኒክ መገምገሚያ መስፈርቶችን በመሙላትና በተለያዩ አራት ፖስታዎች በማሸግ በፖስታው ላይ የፋይነሻል ኦርጅናል እንዲሁም ኮፒ የቴክኒክ ኦርጅናል እንዲሁም ኮፒ መሆኑን በመግለጽ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
9. አሸናፍ ድርጅቶች እንደአስፈላጊነቱ ውል ከመግባታቸው በፍት መ/ቤቱ የጠየቀውን የዕቃ ናሙና ማቅረብ መቻል ይኖርባዋል።
10. ተጫራቾቹ የሚሞሉት የዕቃ ዋጋ ላይ መለኪያና ጥራቱን ጠብቀው መሙላትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
11. በመንግስት ግዥ ላይ እንዳይሳተፍ እገዳ የተጥለው ከሆነ የዕገዳ ጊዜውን ያጠናቀቀ መሆኑን የሚገልጽ መረጃ አያይዝው ማቅረብ መቻል ይኖርበታል።
12. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከወጣው ጨረታ ውስጥ ከብር 200000ብር/ በፊደል/ ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያም በላይ ባለው ግዥ የሚሳተፉ ማነኛውም የሀገር ውስጥ ተጫራች በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለበት።
13. ውል የሚፈጽም ማነኛውም ሰው ውል ለመፈጸም የሚያስችል የህግ ችሎታ ያለው መሆን ይኖርበታል።
14. በዕዳ ያለተያዘ ያልከሰረ ወይም የስራ እንቅስቃሴውን ያላቋረጠ እንዲሁም የንግድ ሥራ እንቅስቃ ያልታገደ ወይም በእነዚህ ምክንያቶች ተከሶ በክርክር ላይ ያልሆነ።
15. የጨረታው አሸናፍ ጨረታን ማሸነፍ በጽሑፍ ከተገለጸለት በኃላ ባሉት ሰባት ቀናት ውስጥ የውል ሰነድ በመውሰድ መፈራረም አለበት፤ ውሉን ከላይ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ቀርበው ካልገባ የጨረታ አሸናፍነቱ ተሰርዘው ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ተወርሰው ለምንግስት ገቢ ይደረጋል።
16. የመድሃኒትና የህኪምና መገልገያ ቁሳቁስ እቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
17. ተጫራቾች በጨረታው ሰነድ , ግልጽ ያልሆነ ነገር ስያጋጥማቸው ማብራሪያ ከፈለጉ በግዥና ንብረት አስተዳደር ሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 02 በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 09 17 00 34 00 / 09 00 94 58 92 / 09 88 91 58 03 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፈለመሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በካፋ ዞን የአዲዮ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-11-11
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቆይቶ ጨረታውን በ16ኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-11 10:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቆይቶ ጨረታውን በ16ኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: South West Ethiopia Region
- Publishing entity: Kaffa Zone Adio Woreda FEDB
- Bid bond: 3%
- Bid document price: 400.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 25, 2026)
- Posted at: 2026-10-26T13:07:00.000Z
- Source: Qelal Tenders