Building Construction
በደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን ለ3B+G+11 ቅይጥ አገልግሎት የሚውል ሕንፃ እና ለB+G+7 ሰንበት ት/ቤት ሕንፃ ፕሮጀክቶች መዋቅራዊ ፍሬም ግንባታ የንድፍ ክለሳ፣ የግንባታ ቁጥጥር እና የውል አስተዳደር የማማከር አገልግሎት ይፈልጋል
Description
ግልፅ ጨረታ
በደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን ለ3B+G+11 ቅይጥ አገልግሎት የሚውል ሕንፃ እና ለB+G+7 ሰንበት ት/ቤት ሕንፃ ፕሮጀክቶች መዋቅራዊ ፍሬም ግንባታ የንድፍ ክለሳ፤ የግንባታ ቁጥጥር እና የውል አስተዳደር የማማከር አገልግሎት የወጣ ግልፅ ጨረታ
(የማማከር ሥራ - አማካሪ መምረጥ)
ሀገር፡ ኢትዮጵያ
የፕሮጀክቱ ስም: - 3B+G+11 ቅይጥ አገልግሎት የሚውል ሕንፃ እና B+G+7 ሰንበት ት/ቤት ሕንፃ ግንባታ
መስፈርቶች፡-
- የደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን የ3B+G+11 ቅይጥ አገልግሎት የሚውል ሕንፃ እና የB+G+7 ሰንበት ት/ቤት ሕንፃ ግንባታ ፕሮጀክቶችን ደረጃ-1 አማካሪ ድርጅት አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል።
- የጨረታው ማስታወቂያ ጋዜጣ ላይ ከወጣ ጀምሮ ለተከታታይ 13 የቀን መቁጠሪያ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን የጨረታው ማስገቢያ የመጨረሻ ቀን በ13ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሲሆን በዛኑ ዕለት 4:30 ይከፈታል።
- ተጫራቾች የግንባታ ሳይቱን እንዲጎበኙ እና ቅድመ ጨረታ ውይይት እንዲያደርጉ ጥቅምት 18 ቀን 2019 ዓ/ም ካቴድራሉ ከጠዋቱ 4፡00 ጨረታውን ከገዙ ተጫራቾች ጋር ስብሰባ የሚያካሄድ ይሆናል።
- የጨረታ ሰነዱን በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 መሣለሚያ የሚገኘው ደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል ካቴድራል ቤተክርስቲያን ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከጠዋቱ 2፡00 - 6፡00 ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ 7፡00 - 11፡00 ሰዓት) የማይመለስ ብር 2,000 (ሁለት ሺ ብር) በመክፈል በአካል ቀርቦ መውሰድ ይቻላል። በተጨማሪም በኢሜል [email protected] ወይም በቴሌግራም DGKamanuel28 (0921876472) የማይመለስ ብር 2,000 (ሁለት ሺ ብር) በካቴድራሉ ልማት ስም በተከፈተው የንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000215809238 በማስገባት የተከፈለበትን ስሊፕ በቴሌግራም በማያያዝ በሶፍት ኮፒ ሰነዶቹን መውሰድ ይችላሉ።
5. ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፦
- የ 2018 ዓ.ም በተቋቋመው ሀገር ህጋዊ እና የታደሰ የንግድ ፍቃድ ወይም የንግድ ድርጅት የምዝገባ ሰርተፍኬት
- ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ለ 2018 ዓ.ም የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት
- ተጫራቾች የT &VAI ተመዝጋቢ ሰርተፍኬት ሊኖራቸው ይገባል።
- ተጫራቾች የታደሰ ህጋዊ የግብር ክሊራንስ ሰርተፍኬት ሊኖራቸው ይገባል።
- በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የመንግስት ግዢ እና ንብረት ባለሥልጣን ዝርዝር የምዝገባ ሰርተፍኬት
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ኦርጅናል ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በተለየ ኤንቨሎፕ በባንክ በተረጋገጠ በካቴድራል ስም ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች ከላይ በተጠቀሱት ተመሳሳይ ፕሮጀክት ሥራዎች ላይ ልምድ ያላቸው መሆን አለባቸው።
አድራሻ፡-
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 መሣለሚያ አካባቢ ደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን፤ የካቴድራሉ አስተዳደር ሕንፃ ግራውንድ ወለል።
ስልክ ቁጥር:- 011-276-3709/ 09 27-28-42-92/ 09 21-87-64-72
የፖስታ ሳጥን 14206፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
ካቴድራሉ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን
Tender details
- Deadline: 2026-11-06
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ13ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-06 10:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ13ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: የደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል ካቴድራል የሰበካ ጉባዔ አስተዳደር ጽ/ቤት
- Bid bond: 50,000.00 ብር
- Bid document price: 2000.00 ብር
- Published on: Reporter (Oct 25, 2026)
- Posted at: 2026-10-26T14:31:56.000Z
- Source: Qelal Tenders