Land Lease & Real Estate

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የዓለም ከተማ ከተማ አስተዳደር መሬት ጽ/ቤት ለመኖሪያ እና ንግድ አገልግሎት የሚውሉ ቦታዎችን በጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል

Description

የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የዓለም ከተማ ከተማ አስተዳደር መሬት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 እንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ 1 መሰረት በ2019 በጀት ዓመት ለ1ኛ ዙር ጨረታ ለመኖሪያ እና ንግድ አገልግሎት የሚውሉ ቦታዎችን በጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል።

1. በመሆኑምመጫረት ለሚፈልግ ማንኛውም ሰው ወይም ድርጅት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እና በኢትዮጵያ ሬዲዮ ከተነገረበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የቦታውን ዝርዝር መረጃና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ።

2. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ማስታወቂያው ከተነገረበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ ይሆናል።

3. ጨረታው የሚዘጋው በአስረኛው ቀን 11፡30 ላይ ይሆናል።

4. ጨረታው የሚከፈተው ከተዘጋበት ቀን ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን 3፡00 ላይ 
ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሲሆን ጨረታው የሚከፈትበት ቦታ በተመለከተ በዓ/ከ/ከ/አስ/መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ነው።

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በዓ/ከ/ከ/አስ/መሬት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 ማግኘት ይችላሉ።

6. የጨረታውን ዝርዝር መረጃ በጽ/ቤቱ የውስጥ ማስታወቂያ መለጠፊያ ሰሌዳ ላይ የሚገለፅ ይሆናል።

7. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በመሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ ፡- ዓለምከተማ ስልክ ቁጥር 011 1320 090
የዓለም ከተማ ከተማ አስተዳደር መሬት ጽ/ቤት



Tender details

  • Deadline: 2026-11-05
  • Bid closing time: 17:30
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እና በኢትዮጵያ ሬዲዮ ከተነገረበት ቀን ጀምሮ በአስረኛው ቀን 11፡30
  • Bid opening: 2026-11-06 09:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እና በኢትዮጵያ ሬዲዮ ከተነገረበት ቀን ጀምሮ በአስረኛው ቀን 11፡30 ታሽጎ ከተዘጋበት ቀን ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን 3፡00
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: የዓለም ከተማ ከተማ አስተዳደር መሬት ጽ/ቤት
  • Bid document price: 500 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Oct 26, 2026)
  • Posted at: 2026-10-27T06:58:36.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders