Printed Advertising Materials

የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን የተለያዩ እቃዎች እና ስራዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 22

የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን ከታች የተገለጹትን

ሎት 1፡- ህትመትና ቦርድ ማስታወቂያ በውል ለማሰራት

ሎት 2፡- የፕሮዳክሽን ስራ ለማሰራት

ሎት 3፡- የኤሌክትሪክ መኪና ኪራይ ለ2019 በጀት አመት ለመከራየት

ሎት 4፡- የግብርና ግብአቶች እቃዎች ለመግዛት

ሎት 5፡- የኮምፒተር፣ ፕሪንተር እና የፎቶኮፒ ጥገና ስራ ለአንድ አመት ውል በማሰር ለማሰራት

ሎት 6፡- የአረንጓዴ አካባቢዎችን እና ፓርኮችን የማልማትና በመንከባከብ ስራዎች በቁርጥ ዋጋ ለማሰራት

ሎት 7፡- የአረንጓዴ አካባቢዎችን እና ፓርኮችን የማልማትና በመንከባከብ ስራዎች በጨረታ ለማሰራት

ሎት 8፡- ትንሿ ጀኔሬተር ለመግዛት

በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም የተጠቀሱትን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራጮች ተጋብዘዋል።

  1. ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ፣የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣የተጨማሪ እሴት በታከስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና ስለግብር አከፋፈል የሚሰጥ ማስረጃ (clearance) ማቅረብ አለባቸው።
  2. ተጫራቾች ለሎት ለእያንዳንዳቸው ሎቶች 20000.00 (ሀያ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ ወይም ባንክ ጋራንቲ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500 /አምስት መቶ ብር/ መገናኛ ዘፍመሽ ፊት ለፊት ታሜጋዝ ህንጻ ላይ ሶስተኛ ፎቅ የፋይናንስ ዳይሬክትሬት ቢሮ ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስር ተከታታይ የስራ ቀን ከጠዋት 2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ በመቅረብ መግዛት ይቻላል።
  4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ፋይናንሻል ዶክመንት ለብቻ እና ቴከኒካል ዶክመንት ለብቻ በማሸግ እና ሁለቱንም ለየብቻ ኮፒ በማድረግ በፖስታ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሳጥኑ እስከሚታሸግበት ከ10ኛው ተከታታይ የስራ ቀን በኋላ በአለው 11ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ድረስ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  5. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ በዚያው ቀን ጠዋት 4፡30 መገናኛ ዘፍመሽ ፊት ለፊት ታሜጋዝ ህንጻ ላይ ሰባተኛ ፎቅ አዳራሽ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል።
  6. የጨረታ መክፈቻው ቀን ቅዳሜና እሁድ ላይ የሚውል ከሆነ በቀጣዩ ሰኞ በተጠቀሰው ሰዓት ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል።
  7. ዘግይቶ የደረሰ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
  8. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 09 15 86 26 36 / 09 23 38 98 72 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

የህዝብ መዝናኛ ቦታዎችና ፓርኮች አስተዳደር ኮርፖሬሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-11-06
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-11-06 10:30
  • Bid opening (note): ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ababa City Administration Public Recreation Areas Management Corporation
  • Bid bond: 20,000.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 26, 2026)
  • Posted at: 2026-10-27T07:06:54.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders