Building Construction
በምሥራቅ ጎጃም ዞን የግንደወይን ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የመሶብ አንድ ማዕከል የቢሮ ግንባታ በግልጽ ጨረታ በጠቅላላ ሥራ ተቋራጮችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በምሥራቅ ጎጃም ዞን የግንደወይን ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የመሶብ አንድ ማዕከል የቢሮ ግንባታ በግልጽ ጨረታ በጠቅላላ ሥራ ተቋራጮችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው።
- የዘመኑን ግብር (ታክስ) የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማያያዝ አለባቸዉ።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው።
- የግዥው መጠን ከብር 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) የምስክር ወረቀት ማያያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ (GC) እና ህንፃ ስራ ተቋራጭ /BC/ ደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ የሆኑ።
- ተጫራቾች በጨረታ ለማሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሠነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የሚሰሩ ስራዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 2,000 (ሁለት ሽህ ብር) በመግዛት የጨረታ ሰነዱን ከመ/ቤታችን ረዳት ገንዘብ ያዥ ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ብር 1,600,000 (አንድ ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዝብ ገቢ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጀዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማለትም ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 25 (ሃያ አምስት) ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ገንዘብ ጽ/ቤት ኃላፊ ቢሮ ቁጥር 12 በ26ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡30 ታሽጐ 4፡00 ላይ ይከፈታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን ተጫራቾች በጨረታው ያወጡት ወጭ መ/ቤቱ ሀላፊነቱን የማይወስድ መሆን ማወቅ ይኖርባቸዋል።
- መ/ቤቱ ጨረታ አሸናፊውን ፋይናሽያልና በቴክኒካል ኢቫሊዩሽን (ግምገማ) ይለያል።
- ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ ቀን ጀምሮ አቤቱታ (ቅሬታ) ካላቸው በተከታታይ 5 (አምስት) የሥራ ቀናት ውስጥ ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ከ5 (አምስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውጭ የመጣ ቅሬታ ጽ/ቤቱ የማይቀበል መሆኑን እንገልፃለን።
- መ/ቤቱ ከአሸናፊ ድርጅቱ ያሸነፋቸውን ሥራዎች 20 በመቶ ከውል በፊት የመጨመር የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ሥራዎች በባለሙያ እየተረጋገጡ ርክክብ የሚፈፀም ይሆናል።
- የጨረታ መክፈቻ ቀኑ በዓል ፣ ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
- ጫረታውን ያሸነፈው አሸናፊነቱ ከተገለጸለት ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ መጥቶ ውል በመያዝ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ ተለዋጭ ካለዉ በመመሪያዉ መሰረት ማስያዝ ይኖርበታል።
- ከአሸናፊው ድርጅት 3 በመቶ የቅድመ ግብር የሚቆረጥ መሆኑን እንገልፃለን።
- ግዥ ፈፃሚው አካል ግዥውን ለመገምገም፣ ለማጽደቅ፣ አቤቱታ ቢነሳ ለማስተናገድ እና ከአሸናፊ ድርጅት ጋር ውል እስከሚገባ ድረስ የመጫረቻ ሰነዱ ጸንቶ የሚቆየበት ለ45 ቀን ይሆናል።
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን በአካል በመገኘት ወይም በስልክ በቁጥር 058 861 26 15 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
የግንደወይን ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-11-20
- Bid closing time: 09:30
- Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ26ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-20 10:00
- Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ26ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: Gindewine City Administration Finance Office
- Bid bond: 1,600,000 (አንድ ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ ብር)
- Bid document price: 2000.00 ብር
- Published on: Be'kur (Oct 26, 2026)
- Posted at: 2026-10-27T07:55:47.000Z
- Source: Qelal Tenders