Transportation Service
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት (EPSS) አዲስ አበባ ቁጥር 1 ቅርንጫፍ ለሠራተኞቹ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት ብቁ የሆኑ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
1. መግቢያ እና የጨረታ ጥሪ
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት (EPSS) አዲስ አበባ ቁጥር 1 ቅርንጫፍ ለሠራተኞቹ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት ብቁ የሆኑ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።
2. የአገልግሎቱ ዝርዝር (Scope of Work)
- የአገልግሎት አይነት: የሠራተኛ ማመላለሻ (ጠዋት እና ማታ)።
- መንገዶች (Routes) ኛ መስመር፡-ሃና ማርያም፣ ሰፈራ፣ ቃሊቲ፣ ገላን፣ ቱሉዲምቱ፣ ቂሊንጦ፣ ኮዬ ፈጬ 2ኛ ሃና፣ ጀሞ፣ አየር ጤና፣ ኬንቴሪ፣ ዘነበወርቅ፣ ቻይና ካምፕ
- የሥራ ቀናትና ሰዓት፡ ከሰኞ እስከ አርብ፣ ጠዋት ከ12፡00 – 2፡30፣ ማታ ከ11፡30 – 1፡00
- የተሽከርካሪ ብዛት፡ ሚኒ ባስ 2 (ሁለት)፡፡
3. የውድድር መመዘኛዎች (Evaluation Criteria)
- የቴክኒክ መመዘኛ፡ የተሽከርካሪዎች ሁኔታ፣ የአሽከርካሪዎች ብቃት እና ልምድ፣ የድርጅቱ ስም እና የሥራ ልምድ።
- የፋይናንሻል መመዘኛ: ለአገልግሎቱ የቀረበው ዋጋ፡፡
- አሸናፊው የሚለየው በቴክኒክ እና በፋይናንሻል ነጥቦች ጥምረት ይሆናል።
የአገልግሎት ግዥ ጨረታ ሰነድ
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት አዲስ አበባ ቁጥር 1 ቅርንጫፍ
ለሠራተኛ ትራንስፖርት ሰርቪስ አገልግሎት ግዥ
የጨረታ ማጣቀሻ ቁጥር፦ 003/2019
የጨረታ ዓይነት፦ ግልጽ ጨረታ
የሰነድ የተዘጋጀበት ቀን፦ 26/01/2019 ዓ.ም.
4. የተጫራቾች ብቃት መስፈርቶች
ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር የሚከተሉትን ማቅረብ አለባቸው፦
1. የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፤
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፤
3. የቫት ምዝገባ ማረጋገጫ፣ ተፈጻሚ ከሆነ፤
4. የግብር ክሊራንስ ሰርተፊኬት፤
5. የተሽከርካሪዎች የሊብሬ ቅጂ
6. የታደሰ የቴክኒክ ምርመራ ማረጋገጫ፤
7. የተሟላ የኢንሹራንስ ሽፋን፤
8. የአሽከርካሪዎች የሙያ መንጃ ፈቃድ፤
9. ተመሳሳይ ሥራ የመሥራት ልምድ ማስረጃ፤
10. የባንክ ሂሳብ መረጃ፤
11. ተጫራቹ በሕጋዊ መንገድ የተቋቋመ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰነድ ፤
12. በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የተፈረመ የጨረታ ማቅረቢያ ደብዳቤ፡፡
5. የተሽከርካሪ መስፈርቶች
የሚቀርቡ ተሽከርካሪዎች፦
- ለሠራተኛ ማጓጓዣ ተስማሚ መሆን አለባቸው፤
- የመቀመጫ አቅማቸው ከተፈለገው የተሳፋሪ ብዛት ጋር መመጣጠን አለበት፤
- በጥሩ የቴከኒክ ሁኔታ መሆን አለባቸው፤
- የመቀመጫ፣ የደህንነት ቀበቶ፣ የብሬክ እና የመብራት ሥርዓት በትክክል መሥራት አለበት፤
- በየቀኑ ንጹህ እና ለተሳፋሪዎች ምቹ ሆነው መቅረብ አለባቸው፤
- አሽከርካሪው የመንገድ ሕግን እና የተቋሙን የደህንነት መመሪያ ማከበር አለበት፡፡
6. የጨረታ ማስከበሪያ
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በተቋሙ በተወሰነው መጠን እና በተፈቀደው የክፍያ መልክ ማቅረብ አለባቸው::
የጨረታ ማስከበሪያ መጠን፦ ብር ያቀረቡትን ዋጋ 10%
- የሚቀበለው ዓይነት፦ የባንክ ዋስትና / ሲፒኦ /
- የሚፀናበት ጊዜ፦ ከጨረታ መክፈቻ ቀን ጀምሮ ባሉት አምስት የሥራ ቀናት።
- የጨረታ ማስከበሪያ ያላቀረበ ተጫራች የጨረታ ሰነዱ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
7. የማቅረቢያ እና የመክፈቻ መረጃ
- የሰነድ መሸጫ ቦታ፦ ሃና ማርያም የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት፣ አዲስ አበባ ቁጥር 1 ቅርንጫፍ ቢሮ ቁጥር 4
- የሰነድ መሸጫ ዋጋ፦ ብር 100 ብር
- የመጨረሻ ማቅረቢያ ቀን፦ 30/02/2019 ዓ.ም.
- የመጨረሻ ማቅረቢያ ሰዓት፦ 8፡00 ሰዓት
- የጨረታ መክፈቻ ቀን፦ 30/02/2019
- የጨረታ መክፈቻ ሰዓት፦ 8፡30
- የመክፈቻ ቦታ፦ ሃና ማርያም የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት፣ አዲስ አበባ ቁጥር 1 ቅርንጫፍ መሰብሰቢያ አዳራሽ
8. የውል ጊዜ
የአገልግሎት ውሉ የሚፀናው ከ30/02/2019 ዓ.ም እስከ 29/02/2020 ዓ.ም. ድረስ ነው::
የውል ማራዘሚያ የሚደረገው በተቋሙ በአገልግሎት ሰጪው አፈጻጸም እና በሚመለከተው የግዥ ሥርዓት መሠረት ብቻ ነው።
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት (EPSS)
Tender details
- Deadline: 2026-11-09
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-11-09 14:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Pharmaceutical Supply Service
- Bid bond: 10%
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 27, 2026)
- Posted at: 2026-10-27T08:26:46.000Z
- Source: Qelal Tenders