Carpets and Curtains

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የጉራጌ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት G+9 ህንፃ አገልግሎት የሚውል መጋረጃ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 05/2019

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የጉራጌ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት G+9 ህንፃ አገልግሎት የሚውል መጋረጃ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡

1. በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣

2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin Number) ያላቸው ፣

4. የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣

5. የግዢው መጠን ከብር 500,000/አምስት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

6. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱትና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች አንድ ኦርጂናልና ሁለት ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣

7. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዕቃ ዓይነት፣ የአምራቹን ስም ፣ የተመረተበትን ዓ.ም በዝርዝር ከዋናው ጋር መያያዝ አለበት ፡፡

8. ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ናሙና ሲጠየቁ ማቅረብ አለባቸው፣

9. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000/አንድ መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተመሰከረለት CPO ወይም ቢድ ቦንድ ወይም ማስያዝ አለባቸው፣

10, ተጫራቾች ከላይ ለተገለታጸው የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ ብር/ በጉ/ገቢዎች መምሪያ በመክፈል ሰነዱን ከጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ግዥ/ንብ/አስ/የሥራ ሂደት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፣

11. ማንኛውም ተጫራች ዕቃውን ጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ወልቂጤ ከተማ ድረስ ለማቅረብ የሚያስችል ዋጋ የሚያሳይ የጨረታ ሰነድ ኦሪጅናልና ኮፒ በማለት በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በጥንቃቄ ታሽጐ ይህ ማሰታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት ጉራጌ ዞን ፋ/መምሪያ ግዥ ንብ/አስ/የሥራ ሂደት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡30 ድረስ ማስገባት አለባቸው፣

12. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት የጨረታ ሰነዱ ታሽጐ በዚህ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ አዳራሽ በይፋ ይከፈታል፣

13. የጨረታው ማስከበሪያ /ሲፒኦ/ ቢድቦንድ በጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ስም መሰራት አለበት፡፡

14. መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤

15, ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ወደሚቀጥለው ቀን የሚሸጋገር መሆኑን እናሳስባለን፡፡

16, ለበለጠ መረጃ መ/ቤቱ ድረስ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0113 300 112 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፣

ማሳሰቢያ፦ ለጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ የምታቀርቡ 90 ቀንና ከዚያ በላይ የሚቆይ መሆን አለበት፡፡

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የጉራጌ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-10
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ይህ ማሰታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-11-10 14:30
  • Bid opening (note): ይህ ማሰታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
  • Region: Central Ethiopia
  • Publishing entity: በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የጉራጌ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት
  • Bid bond: 100,000.00 ብር
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 26, 2026)
  • Posted at: 2026-10-27T10:31:35.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders