Vehicle

በላይነህ ክንዴ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ ወደ ተለያዩ የግንባታ ፕሮጀክት ሳይቶች የኮንስትራክሽን ግብዓቶች (ጭነት) የሚያጓጉዙ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የትራንስፖርት አገልግሎት መግዛት ይፈልጋል

Description

በድጋሚ የወጣ የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ

በላይነህ ክንዴ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ ወደ ተለያዩ የግንባታ ፕሮጀክት ሳይቶች የኮንስትራክሽን ግብዓቶች (ጭነት) የሚያጓጉዙ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የትራንስፖርት አገልግሎት መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው እና በቂ ተሽከርካሪዎችን ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ትራንስፖርተሮች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል፦

1. ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

2. ተጫራጮች የጨረታ ሰነዱን ከድርጅታችን ግዥ ክፍል መውሰድ ይቻላሉ።

3. ተጫራቾች የጨረታ ማስረከቢያ ዋጋቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው።

4. ጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) የጠቅላላ ዋጋው 10 ፐርሰንት ሆኖ ከብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺ ብር) ያልበለጠ መሆን አለበት። የጨረታ ማስከበሪያው በጥሬ ገንዘብ፤ በቼክ ወይም ባንክ በተመሰከረለት ሲ.ፒ.ኦ፤ ለብቻ በአነስተኛ ፖስታ በሰም በታሸገ ዋጋ ማቅረቢያ ወይም ፕሮፎርማ ኢንቮይስ መቅረብ ይኖርበታል፤

5. ከላይ ከተጠቀሱት ማስረጃዎች እና ሌሎችም ተወዳዳሪዎች ለውድድር ይጠቅመኛል የሚሏቸው ማስረጃዎች መቅረብ ይችላሉ።

ከላይ የተጠቀሱት ሁሉም ማስረጃዎች በትልቅ ፖስታ ውስጥ በሰም ታሽገው እና ማህተም አርፎስባቸው መቅረብ እና አራት ኪሎ፤ አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ህንጻ የምድር ወለል በሚገኘው የድርጅቱ ቢሮ እስከ ጥቅምት 26 ቀን 2019 ዓ.ም ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን አስመዝግበው እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ማስገባት አለባቸው።

የጨረታ ሳጥኑ ጥቅምት 26 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራጮች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። አሸናፊዎች ጨረታውን ማሸነፋቸውን ድርጅቱ ከአሳወቀ ጀምሮ ባሉት አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ውል መያዝ አለባቸው። በተጠቀሰው ጊዜ ውል ካልያዙ የጨረታ ማስከበሪያው ገንዘብ ተመላሽ አይሆንም። ድርጅቱ

የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ድርጅቱ


Tender details

  • Deadline: 2026-11-05
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-11-05 14:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: በላይነህ ክንዴ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ
  • Bid bond: 10 ፐርሰንት ሆኖ ከብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺ ብር) ያልበለጠ መሆን አለበት
  • Published on: Reporter (Oct 28, 2026)
  • Posted at: 2026-10-28T09:07:09.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders