Food and Beverage
በልደታ ክ/ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት የምግብ፣ የውሃ፣ የመኝታ እና የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 02/2019
በልደታ ክ/ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት ስፖርት ምክር ቤት ግዥ ቡድን በግልፅ ጨረታ ቁጥር 02/2019 ዓ.ም ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት በሀዋሳ ከተማ የምግብ የውሃ የመኝታ እና የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ሎት፣1 ለወንድ ስፖርተኞች እና ለኮቺግ ስታፍ የምግብ ፣ ውሃ እና የመኝታ አገልግሎት ግዥ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000.00
- ሎት 2. ለወንድ ስፖርተኞች የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ የጨረታ ማስከበሪያ ብር10,000.00
1. ተጫራቾ የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት በልደታ ክ/ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን በመቅረብ ለእያንዳንዱ ጥቅል የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
2. ተጫራቾች፡-
ሀ. በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው
ለ. የተጨማሪ እሴት ታስክ የተመዘገበ ፣ታክስ ክሊራንስ እና ቲን ነምበር ማቅረብ የሚችል።
3. በየሎቱ በተቀመጠው መሠረት የጨረታ ማስከበርያ የብር መጠን (CPO) “የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ምክር ቤት “ በሚል ስም በማሰራት ከሰነዱ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነድ ውስጥ በሚገኘው የዋጋ ማቅረቢያ ላይ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ የተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በልደታ ክፍለ ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
5. ለጨረታ ከቀረቡት አገልግሎቶች ዝርዝር ውስጥ ጽ/ቤቱ 25 ጨምሮም ሆነ ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።
6. ተጫራቾች በጨረታው ቢያሸንፉ ሊያቀርቡ የሚችሉትን አገልግሎቶች ናሙና ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን፣ በጨረታው አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት አሸናፊነቱ ተገልፆ በሚሰጠው የግዥ ትዕዛዝ መሠረት አገልግሎቶችን ቀደም ሲል አቅርቦት በተመረጠው ናሙና መሠረት ለመ/ቤታችን ማቅረብ አለበት።
7. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በመጨረሻው ቀን ከቀኑ 10፡30 ሰዓት ታሽጎ በማግስቱ ከጠዋቱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
8. ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ- በልደታ ክ/ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ስልክ ቁጥር 011 872 2106
አዲስ አበባ ልደታ ክ/ከተማ መሬት አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አጠገብ ወይም በላይ ተክሉ ኬክ ቤት አጠገብ 5ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 502
በልደታ ክ/ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-11-10
- Bid closing time: 16:30
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በመጨረሻው ቀን ከቀኑ 10፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-11 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በመጨረሻው ቀን ከቀኑ 10፡30 ሰዓት ታሽጎ በማግስቱ ከጠዋቱ 4፡00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Lideta Sub City Design and Building Works Administration Finance Office
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ
- Published on: Addis Zemen (Oct 30, 2026)
- Posted at: 2026-10-30T07:06:54.000Z
- Source: Qelal Tenders