Construction Machinery
የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ለአዳማ-አሰላ፣ ጨፌ ዶንሳ፣ ለአዲስ አበባ እና ሃረር መንገድ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የኮንስትራክሽን ማሽነሪ መሳሪያዎችን በክፍት ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር EEC/NCB/ OP/02/2026
የተለያዩ ማሽነሪ መሳሪያ መከራየት በክፍት የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ለአዳማ-አሰላ፣ ጨፌ ዶንሳ ፣ለአዲስ አበባ እና ሃረር መንገድ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ የኮንስትራክሽን ማሽነሪ በዚህ ዘርፍ ከተሰማሩ አቅራቢ ድርጅቶች በክፍት ጨረታ አወዳድሮ በመምረጥ መከራየት ይፈልጋል።
- ተጫራቾች አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናችውን የሚያሳይ የምስክር ወረቀት የሚያቀርቡ ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለሥልጣን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ጨረታው የሚከናወነው በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞከራያዊ ሪፐብሊክ መንግስት የግዥ አፈፃፀም ሕጎች እና የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የግዥ መመሪያ በተገለጸው የክፍት ጨረታ ሥነ ሥርዓት መመሪያ መሠረት ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 15,000.00(አስራ አምስት ሺህ ብር) (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ (Unconditional Bank Guarantee, የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ማሰራት አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከዚህ በታች በተገለፀው ቢሮ በመቅረብ 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
- የዕቃው ዝርዝር እና አገልግሎቶቹ ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች (specification)ተያይዟል።
- ማንኛውም ተጫራች በሌላ የጨረታ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም።
- ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርበው ዋጋ ቢያንስ ሶስት ወር የሚጸና መሆን አለበት።
- ተጫራቾች የቴክኒክ ሰነድ እና የፋይናንሻል ሰነዳቸውን ለየብቻ ማዘጋጀትና በአንድ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ጨረታው ኅዳር 1 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ኅዳር 1 ቀን 2019 ዓ.ም ከጥዋቱ በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ በሚገኝበት ከዚህ በታች በተገለፀው አድራሻ ይከፈታል።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን ሙሉ አድራሻቸውን፣ ፊርማቸውን እና ድርጅታቸውን ማህተም ማስፈር አለባቸው።
- ጨረታው የቴከኒክ መስፈርቱን ካሟሉት አቅራቢዎች መካከል ዝቅተኛ ዋጋ ላቀረበው ተጫራች አሸናፊ ይደረጋል።
- መ/ቤቱ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- የኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (ኢ.ኢ.ኮ) ሕንጻ ) ሁለተኛ ፎቅ፣ የግዥ ንብረትና ፋሲሊቲአስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቡድን ቢሮ የቀድሞ ኢምፔሪያል ሆቴል ፊት ለፊት ቦሌ ክፍለ ከተማ
ወረዳ 05 ስልክ ቁጥር +251-924-053-307/+251-11 897-469/+251-922-346-904
የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን
Tender details
- Deadline: 2026-11-10
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-11-10 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Engineering Corporation
- Bid bond: 15,000.00 ብር
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 29, 2026)
- Posted at: 2026-10-30T07:54:56.000Z
- Source: Qelal Tenders