Vehicle

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ለ2019 በጀት ዓመት ለመንገድ ግንባታ እና ጥገና ስራ የሚያገለግሉ ገልባጭ መኪኖች በመከራየት ማሰራት ይፈልጋል

Description

የገልባጭ መኪና ኪራይ አገልግሎት
የቁርጥ ዋጋ ግዥ ጥሪ ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ለ2019 በጀት ዓመት ለመንገድ ግንባታ እና ጥገና ስራ የሚያገለግሉ ገልባጭ መኪኖች በቁርጥ ዋጋ ከዚህ በታች የተቀመጡትን መስፈርች ከሚያሟሉ አከራዮች በመከራየት ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁ

 

የአገልግሎት ዓይነት

 

የስሪት ዘመን

ዝቅተኛ የመጫን አቅም

ልኬት

 

ዋጋ ነዳጅ እና ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ

የሚፈለግ የመኪና ብዛት

1

የገልባጭ መኪና ኪራይ

 

>2013 G.C

>12 ሜ.ኩ

 

M3/km

42.27

 

146

 

Ton/km

 

41.20

 

1. አከራይ አግባብነት ያለው ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ፣የንግድ ምዝገባ ፍቃድ ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ፤የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ እንዲሁም በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረ-ገፅ ላይ በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡበትን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

2 የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ ኦርጅናልና ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

3. መመዝገብ የሚችሉት የተሸከርካሪው ባለቤት ወይም በስማቸው ተሽከርካሪውን ማከራየት እንደሚችሉ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ ህጋዊ ውክልና የሚያቀርቡ ብቻ ናቸው፡፡

4. አከራይ እንዳመጣጣቸው ቅደመ ተከተል ተመዝግበው በቅድም ተከተሉ መሰረት ለስራው ይጠራሉ፡፡

5 ለኪራይ የቀረበው ገልባጭ መኪና የቴክኒክ ይዘት ከላይ በተጠቀሱት መስፈርት መሰረት ስለመሆኑ የባለስልጣን መ/ ቤቱ እያረጋገጠ ስምሪት የሚሰጥ ይሆናል፡፡

6. በአገር አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋ ከ15% በላይ ሲጨምር የውል ዋጋ ማሻሻያ ይደረጋል፡፡ በተመሳሳይ የነዳጅ ዋጋ ቅናሽ በሚኖርበት ወቅት የተደረገው የዋጋ ልዩነት አቅራቢው ወይም አከራይ ድርጅት ለባለስልጣን መ/ቤቱ ተመላሽ የሚያደረግ ይሆናል፡፡ የነዳጅ ጭማሪ ማሻሻያ ለማድረግ አማካይ የመጫን አቅም ልኬት 16.74 ይሆናል፡፡

7. የስራ ቦታ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በሚገኙ የባለሥልጣን መ/ቤቱ ፕሮጀክቶች ይሆናል፡፡

8 ገልባጭ መኪናው ጂፒኤስ የተገጠመላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ክፍያ መኪኖቹ በተጓዙበት ርቀት መሰረት ብቻ የሚፈጸም ሲሆን የጉዞ መነሻና መድረሻ ኪ.ሜ (odometer) ንባብ እና ከGPS የሚገኝ መረጃ መሰረት ትክክለኛው ምልልስ ይረጋገጣል፡፡

9. የውል ቆይታ ጊዜ ውል ከተፈረመበት ጊዜ ጀምሮ እስከ መስከረም 30 ቀን 2020 ዓ.ም ድረስ ይሆናል፡፡

10. አከራይ የገልባጭ መኪኖች ጂፒኤስ (GPS) ቢቋረጥ አከራይ በሁለት ተከታታይ ቀናት ውስጥ ጠግኖ ወደ ስራ ማስገባት ያለበት ሲሆን ጂፒኤስ (GPS) ብልሽት የቆመበትን ጊዜያት ብልሽቱ ከተከሰተ ጀምሮ ባለት ሁለት ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ለባለስልጣን መ/ቤቱ በደብዳቤ ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡ አከራዮች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ወይም በሬዲዮ ጥሪ ከተላለፈበት ቀን ጀምሮ በስራ ቀን እና ሰዓት ሳርቤት በሚገኘዉ የባለስልጣኑ ዋና መ/ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 022 ለምዝገባ የሚስፈልጉትን ማስረጃዎች ኦርጅናልና ኮፒ ይዘው በመቅረብ መመዝገብ ይኖርባቸዋል፡፡

ባለስልጣን መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ የኪራይ አገልግሎቱን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ስ.ቁ 011-3-72-28-25/
ሳርቤት ፑሽኪን አደባባይ
አዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን


Tender details

  • Deadline: 2026-11-16
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): የጨረታው መዝጊያ ቀን እና ሰዓት አልተገለጸም
  • Bid opening: 2026-11-16 12:00
  • Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀን እና ሰዓት አልተገለጸም
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ababa City Roads Authority
  • Buyer's registered address: አዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ሳር ቤት ፑሽኪን አደባባይ ሳይደርስ
  • Published on: Addis Zemen (Oct 31, 2026)
  • Posted at: 2026-10-31T07:24:20.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders