Building Construction
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስልጤ ዞን የወራቤ ከተማ አስተዳደር ስራ ዕድል ፈጠራ እና ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት ለሚሰራው የሼድ ግንባታ GC-5/ BC-5 እና ከዛ በላይ በጨረታ አወደድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስልጤ ዞን የወራቤ ከተማ አስተዳደር ስራ ዕድል ፈጠራ እና ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት ለሚሰራው የሼድ ግንባታ GC-5/ BC-5 እና ከዛ በላይ በጨረታ አወደድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም -
- በመስኩ የንግድ ፍቃድ ያላቸው
- የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የምትችሉ በመንግስት ግዢ ለመሳተፍ የአቅራቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ የምትችሉ
- የጨረታ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ 100,000 ማስያዝ የሚችሉ
ተጫራቾች ሰነዱን ከወራቤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በመምጣት የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500 /ሶስት መቶ ብር/ብቻ በመክፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን የጨረታ ሰነዱን አንድ ኦርጅናል ቴክኒካል ኦርጅናል ፋይናሻል እና ሁለት ቴክኒካል እና ፋይናሻል ሁለት ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 20/ሃያ/ ተከታታይ ቀናት በኋላ ባለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በጽ/ቤቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 መገኘት በሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ፡ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡የተሞላው ዋጋ መግለጫ ካልተሰጠበት ከነቫት ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
ለበለጠ መረጃ 046 771 0211 ይደውሉ፡፡
በስልጤ ዞን የወራቤ ከተማ አስተዳደር የሥራ ዕድል
ፈጠራ እና ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-11-20
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 20/ሃያ/ ተከታታይ ቀናት በኋላ ባለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-20 10:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 20/ሃያ/ ተከታታይ ቀናት በኋላ ባለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Central Ethiopia
- Publishing entity: Central Ethiopia Job Opportunity Creation Enterprise Bureau
- Bid bond: 100,000 ብር
- Bid document price: 500 /ሶስት መቶ ብር/
- Published on: Addis Zemen (Oct 31, 2026)
- Posted at: 2026-10-31T07:52:51.000Z
- Source: Qelal Tenders